የለፋንበትን ገንዘብ ሰርቆ የጠፋውን ሰው ለህግ እንድናቀርብ አግዙን
የፒቲሽኑ አላማ በዋነኝነት 47 ህጋዊ ማስረጃ ያለን በኤሜሬትስ የምንኖር ሴት የሰው ቤት ተቀጣሬ እህቶች ነን።የደረሰበን በመጭበርበር እና መከዳት በሞራል ህገወጥ በመሆን ካርጎ አደርጋለሁ በማለት ፖስፖርት አድሳለሁ በማለት ቪዛ እሰራለሁ ትኬት ወደ ኢትዮጵያ እቆርጣለሁ ወደ ኢትዮጵያ በህጋዊ መንገድ ገንዘብ እልካለሁ በማለት የተለያዩ የሌብነት ሲስተሞችን በመጠቀም መጀመሪያ ከስንታየሁ ወደ ሮቤል ባለማህተቡ የቲክቶክ አካውንቱን በመቀየር በሃይማኖት ሽፋን ፍጹም ማስመሰል በተሞላበት መንገድ የሰውን አመኔታ ለማግኘት የተለያዩ መንፈሳዊነት ያላቸውን ቃላት በመጠቀም እና በማስመሰል የተለያዩ መዝሙሮችንም በመዘመር የሰውን እምነት ካገኘና በሰዎች ዘንድ እርዱኝ እንተባበር ኢንተርናሽናል ቢሮ ከፍቻለሁ እኔም ተጠቅሜ እናንተምንም ልጥቀማችሁ ኢትዮጵያ ዊ ወንድማቹ ክርስቲያን የተዋህዶ ልጅ ነኝ እያለ በድፍረት እዚህ ያሉ የተለያዩ ቲክቶከሮች ጋር በመሄድ ታማኝ ቅን ሰው ነኝ ስራዬን አስተዋውቁልኝ ብሏቸው እነሱም አስተዋውቀውለት ህዝቡም አምኗል ጥሩ ሰው ለስራው ታማኝ ነው ህጋዊም ነው ህጋዊም ቢሮ አለው ብለን የብዙዎቻችንን ብር ይዞ ወደ አውሮፖ ገብቷል። እዚህ ኤመራት ውስጥ የምንኖር እኛ ሴት የቤት ሰራተኞች ቤተሰቦቻችንን የምናስተዳድር የታመሙ ቤተሰቦቻችን ማሳከም እና ልጆቻችን ለማስተማር ለመኖር ብር እንዲልክልን በህጋዊ አካውንቱ ብራችንን አስገብተንለታል።በኦንላይን ቪዛ ለማደስ ደግሞ ወፈረፋ ሄዳችሁ ከምትጠብቁና የማይፈቀድላችሁ ለመውጣት አሳድስላችሃለሁ ብሎ ብሩንም ፖስፖርታቸውንም ወስዷል። ቪዛ እሰራላችሃል ብሎ ብዙ ታማሚ ህክምና የሚያስፈልጋቸው አስቀድመው አደራ ብለው ህክምናዬ እንዳይቋረጥ ህገወጥ መሆን አልፈልግም ብለው እየለመኑት ብራቸውንም የቪዛ ዶክመንታቸው አበላሽቶ ነው የሄደው ካርጎ እልካለሁ ብሎ ብራቸውን እቃቸውንም ወስዷል። ከፊርማ ማሰባሰቢያው የምንፈልገው ይሄ ሰው ሞራላችን ግዚያችንን ሴትነታችንን ገንዘባችንን ህገወጥ አድርጎናል ቤተሰባችንን እንዳያምኑን እንዲጠራጠሩን እና እንዲጠሉን አድርጎናል በሱ ብር አለማድረስ ምክንያት ባለመታከማቸው ቤተሰባቸውን በሞት ያጡ እህቶች ስላሉ ለህግ ባለበት አገር በሌብነት እና በማጭበርበር ወንጀል ለህግ እንዲቀርብልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።
Comment