Skip to main content
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

527 signatures 223 to reach 750
ኪዳነ ማ. signed
G
Gebremariam signed
ጀግኔ መ. signed
ወለተ ሚ. signed
D
DANIEL A. signed
S
Someone signed
A
achamyeleh signed
M
Marth M. signed
G
Girma W. signed
M
meskerem signed
TB
Started by Tewodros Birhanu 10 years, 10 months ago







የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት

ቀን 14/01/2008

ቁጥር 00/68/ማ/ህ/2008

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- በተሀድሶ መናፍቃን ላይ የወጣ የተቃውሞ የአቋም መግለጫ፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብዙ የመከራ ዘመናትን አሳልፋለች ቀጥሎም ብዙ ዘመናትን ተሻግራ ይኽኛውን ትውልድ ታስተምራለች ምክንያቱም ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት ስለሆነች ነው፡፡

ንጽህት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት መሆኑ በመጽሐፍ ቅድስ ተጽፏል፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከጠላት ውጊያ ተለይታ የኖረችበት ዘመን የለም ወደፊትም አትኖርም መሰረቷ አይናወጥምና፡፡ እነዚህን የመከራ ዘመናትን ባለጊዜው ትውልድ ለችግሮቹ መፍትሔ እያበጀ መስዋእትነትን እየከፈለ እዚህ ዘመን ላይ እንዲደርስ የግዴታውን ተወጥቷል፡፡

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀደምት አበው ግዴታቸውን ተወጥተው ማለፋቸውን ከእናንተ ተምረናል፡፡

በዚህ ዘመን ያላችሁ አባቶቻችን ቤተክርስቲያን የማስተዳደር ግዴታው ኃላፊነቱ በእናንተ ላየ እንደተጣለ ስለምናምን ነው፡፡ ነገር ግን በምዕመናን መካከል ከዶግማ ጀምሮ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ እየተፋለሰ በመሆኑ የሰልስቱ ምዕት ትምህርት ቀርቶ የሉተር አስተምህሮ በሰፊው እየታየ ነው፡፡

ስለዚህ የቀደሙት አባቶቻችን ልጆች እንደመሆናችሁ እኛ ደግሞ የእናንተ ልጆች እንደመሆናችን ከጥቅምት 12 ቀን የሚጀመረው መንፈስ ቅዱስ ለሚመራው ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እግዚአበሔር መርጦ የሾማችሁ ባለአደራ አባቶቻችን ከእኛ ከልጆቻችሁ ከምዕመን የሚቀርበውን ኃይማኖታዊ ጥያቄ ተመልክታችሁ ውሰኔ እንድትሰጡን ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም በትህትና እንጠይቃለን፡፡

ጥያቄ

  • ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ በፊት ውግዘት ያስተላለፈባቸውን ግለሰቦች ሆኑ ማህበራት ለምዕመን በግልጽ በሚዲያ እንዲተላለፍ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
  • ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምሮ ውጭ የምንፍቅና ትምህርት የሚያስተላልፉትን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊት የሚያፋልሱትን በተሳሳተ መንገድ እያስተማሩ ያሉ ሰዎች እንዲወገዙልን፡፡
  • የቤተክርስቲያኒቷ ሦስቱን መንፈሳዊ ኮሌጅ መናፍቃን ባልታወቀ መንገድ ሰርገው ስለገቡ እነዚህን መርምራችሁ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ የሚያስተምሩ መምህራኖችን እንዲሁም የኦርቶዶክስ ልጆች የሆኑ ተማሪዎች ብቻ እንዲማሩ እንዲደረግልን፡፡
  • የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሚለው ስያሜ በቤተክርስቲያኒቱ ሥርዓት ከቅዱስ ሲኖዶስ ፍቃድ ያላገኙ ከኢትዮጵያ ውጭ በአውሮፓ፣ በአፍሪካ በአረብ ኤምሬት የእምነት ተቋም ነን የሚሉ እንዲዘጉልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን፡፡
  • የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮ የሚያፋልስ የህትመት ውጤቶች ሲዲ፣ መጽሐፍ፣ መጽሔት እንዲወገዙ በትህትና እንጠይቃለን ወደፊትም ማንኛውም የህትመት ውጤት ያለቤተክርስቲያን ፈቃድ እንዳይታተሙ እንድታደርጉ እንጠይቃለን፡፡
  • ኢ.ቢ.ኤስ የሚዲያ ጣብያ የሚተላለፍ ታኦሎጎስና ቃለ አዋዲ የተሰኙ የቴሌቪዥን መርሃ-ግብሮች በቤተክርስቲያኒቱ ስም ምንፍቅናን እየዘሩና የቤተክርስቲያኒቷን ክብር እየነኩ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ይኽን ተመልከቶ ስርጭታቸው እንዲያሳግድልን እንጠይቃለን፡፡

በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኒቷ ከላይ የገለጽናቸውን ችግሮች ሲኖዶሱ በትኩረት ተመልክቶ ውሳኔ እንዲሰጥልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን፡፡

‹‹የቀረውን ነገር ሳልቆጥር እለት እለት የሚከብደኝ የአብያተክርስቲያናት ሁሉ ሀሳብ ነው፡፡››

2ኛ ቆሮ. ፲፩፡፳፰

ብሯኪያችሁ ይደርብን፡፡

እግዚአብሔር ሀገራችንን እና ቅድስት

ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- +251 911355038/+251911860603

Updates

October 10, 2015

We have reached five hundred signatures on this submission. I am finalizing the formal request to be delivered to the Holy Synod office for review.

Reached 500 supporters

October 10, 2015

October 9, 2015

The scale of this response confirms the urgency of the matter and we are now moving to consolidate these signatures into a formal document for delivery. Our representatives are finalizing the meeting request with the Holy Synod office to ensure this submission is formally recognized and addressed.

October 2, 2015

We have reached one hundred signatures which establishes the necessary foundation to proceed with our formal request. I am currently coordinating with legal counsel to finalize the submission documents for the Holy Synod office.

Reached 100 supporters

October 2, 2015

319 Comments

A
Abel Wolkeba
10 years ago Featured

'ከዝምታዬ የተነሳ እንደ ዲዳ ሆንኩ' እንዳለ ቅዱስ ዳዊት የቅዱስ ሲኖዶስ ዝምታን ከምን ልበለው:: አባቶች ሆይ በጎቻችሁ እረኛ ከማጣት ተቅበዘበዝን:: የነብስ አባቶቻችን ስትሆኑ ለስጋ እረኞች አሳልፋችሁ አትስጡን:: እኛም እንደ ሆሴህ ዘመን ሰዎች ዕውቀት ከማጣታችን የተነሳ ጠፍተናል:: ለስጋችን ሳይሆን ለነፍሳን በለመለመ መስክ አሰማሩን:: ያኔ ለነፍስ የተሰጠ ለስጋም ይተርፋል::

Y
Yordanos Kebede
10 years ago Featured

አምላከ ቅዱሳን ይፈርዳል እርሱ ሁሉንም ያያል ዝም ያለ አይምሰላችሁ እርሱ ዘቤቱ ቀናተኛ ነውና ዝም አይልም የሚናገርባት የሚፈርድበት ቀን ይመጣል፡፡ ቤተክርስቲያን ስትደፈር ስትፈርስ ቆሞ የሚያይ ትውልድ አይኖርም ቃላችንን ሰጥተናል ቤተክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ አምላከ ቅዱሳን ሁላችንንም በቤቱ ያጽናን

T
Tigist abera
10 years ago Featured

በአይማኖታችን እና በቤተክርቲያን ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና እንቅስቃሴ ማድረግ የቤተክርቲያናችንን ቀኖና እና የቤተ የቤተክርቲያናችንን ስርዓት ወዳልተፈለገ አላማ ስለሚወስድ በአስችኳይ ህገ ወጦች ሥራችውንና ድርጊታችውን እንዲያቆሙ እንጠይቃለን ቅዱስ ሲኖዶሱም ለቤተ ክርስቲያን ጠንቅ የሆኑትን ጉዳዮች እንዲያወግዝልን እንጠይቃለን ኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር።

M
mekdas kebede
10 years ago Featured

ስለም እግዚአብሔር ከሁላችሁም ጋር ይሁን እኔ በተሀድሶዙርያ ላይ በጣም አዝኛለሁ እንደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶእነቴ እግዚአብሔር አምላክ ወደልባችው እንድመልሳችው የዘወትር ፀሎትነው በሚሉት ነገር ክብር ይግባትነ በወላድት አምላክ አታማልድም ቅዱሳኑ አያማልዱም ቤትክርስቲያን ትታደስ በሚሉት ሁሉ ልቤ ተስብሮዋል እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋልን ይስጣችው ነው የምለው እንደነዚህ አይነት የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ ተኩላወች እግዚአብሔር አምላክ በኪነ ጥበብ ይታደገን አሜን

H
Hayimanot tesfaye
10 years ago Featured

ቡራኪያችሁ ይድረሰን አባቶቻችን በ EBS የሚተላለፉ ቃለ አዋዲ እና ታኦሎጎስ የሚል ስርጭት እውነት ነው ይዘጋልን፡ ፡ በዱባይ የሚያገለግሉትንም እርምጃ ይወሰድልን ብዙ ነፍሳት እየጠፉ ነውና ሲኖዶሱ ከምንም ነገሮች በላይ በአሁኑ ስብሰባቸው የተሃድሶችን ጉዳይ በስፋት ቢመለከተው እንላለን ሰላም

K
Kahsay Hailu
10 years ago Featured

ታኦሎጎስና ቃለ ኣዋዲ መዘጋት ኣለባቸው። በቅዱስ ሲኖዶሱ ያሉ ህፀፅ ይሚታይባቸ ኣባቲች ሃገርና ትውልድ ሳያበላሹ ሊገሰፁና ሊወገዙ ይገባል። ባጠቃላይ ከቅድስት ቤተክርስትያኒቱ ዶግማ፥ ቀኖናና ትውዲት ብሎም ቅላፄ ውጪ የሆኑ ሁሉ በሽታቸው ይታወቃሉና ቅዱሳን ኣባቶች በፆምና በስባኤ መርምረው መፍትሄ እንዲያስቀምጡ እላለሁ።

ኪዳነ ማርያም
2 years ago

እምዬ ኦርቶዶክስ

G
Gebremariam
3 years ago

ከ ቀኖና ቤተክርስቲያን ዉጪ ሰልጣን ክህነት አይኑር::

Help this petition grow

Share it with friends to help reach 750 signatures.

Sign Petition

We never post to your account. Social sign-in is used only to verify your signature.

or sign with Email

Add a comment?

Your signature will be added via . Tell others why you're signing — it's optional.

By signing, you accept iPetitions Terms of Service and Privacy Policy.

Share Petition

Don't stop at signing, share the petition link with friends to multiply our impact

Copy link or share directly

Instagram
QR Code