Skip to main content

Urgent Appeal on Government Induced Division s, Necropolitical Policies and Threat of Ethnic Cleansing and Religious Genocide Against Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

6 signatures 44 to reach 50
S
Seblewongel A. signed
G
Gedeon T. signed
S
Samson D. signed
B
Brook A. signed
G
Gebretsadik T. signed
M
Moa T. signed
MT
Started by Moa Tewahedo 1 month, 3 weeks ago

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ፈተናዎችን እያለፈች ከዘመናችን የደረሰች ክርስቶሳዊ ቤታችን ናት። ታሪክ እንደሚመሰክረው በየዘመናቱ የደረሰባት መከራ እና ስደት የራሱን ጠባሳ እየተወ አልፏል። ሆኖም ያለፈው ችግር ለአዲሱ ችግር መሠረት እና መደላድል እየሆነ መከራ እና ስደቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ እና እየባሰ እንዲሄድ አድርጎታል። ከሃምሳ እና ስድሳ ዓመታት ወዲህ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሰ ያለው ፈተና በዓይነቱም በይዘቱም እጅግ የተለየ እና የከፋ ነው። በተለይ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የሀገሪቱ ገዢ አካል ወደ ሥልጣን ከመጣጀምሮ እየወረደባት ያለው የመከራ ዶፍ በሕልውና ስጋት አፋፍ ላይ እንድንቆም አድርጎናል። ሆኖም በደሙ የመሠረታት ጌታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ኃይል አድርገን በአንድ ላይ ከቆምን በመድኃኔዓለም ኃይል ከአሸናፊዎች ሁሉ እንበልጣለን። ለዚህም ምሥክሮቻችን በእሳት ወላፈን እና በዉሀ ማዕበል መካከል እያለፉ ሕያው የታሪክ ዓምዶችን ያቆሙልን ጽኑዓን አባቶቻችን እና እናቶቻችን ናቸው። ዛሬ የታሪክ ተረኞቹ እኛ ነን። ይህንን ስጋት ወደ ድል ለመቀየር ተባብረን እንነሣ በሚል መንፈሳዊ ሕሊና የህንን ጉዳይ ጉዳያቸው አድርገው ሊያዩ ለሚችሉ ዓለም አቀፍ እና አሕጉራዊ ተቋማት ድምጻችንን ለማሰማት ትብብራችንን እና አንድነታችንን በፊርማችን እንድንገልጽ ይህ የፊርማ ማሰባሰቢያ ገጽ በሞዓ ተዋሕዶ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። ማናችንም ለራሳችን ከፈረምን በኋላ ቢያንስ ሰባት ሰው እንድናስፈርም ስለሃይማኖታቸው ሰማእትነት እየተቀበሉ ባሉት ወገኖቻችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ሞዓ ተዋሕዶ

ሰኔ ፲፭ ቀን ፳፻፲፰ ዓመተ ምሕረት 

2 Comments

B
Brook Alador Verified
1 month ago Featured

I’m an Ethiopian Orthodox Tewahedo faith believer. It’s sickening to see our Ethiopian Orthodox tewahedo faith followers persecuted, displaced and churches burn.

S
Samson Daniel Verified
1 month ago

The genocidal regime in Ethiopia led by fascist Abiy Ahmed Ali is responsible for the genocide against the Amhara community Orthodox Christian.

Help this petition grow

Share it with friends to help reach 50 signatures.

Share Petition

Don't stop at signing, share the petition link with friends to multiply our impact

Copy link or share directly

Instagram
QR Code