Skip to main content

we did it and honestly i still cant believe it. the plans for the factory in the monastery have been stopped and i am so thankful to everyone who stood up for waldiba. take a moment to celebrate this win because we really proved that keeping the history and spirit …

June 10, 2012

የኢትዮጵያ ገዳማት ህልውና ይከበር!

የኢትዮጵያ ገዳማት ህልውና ይከበር!

🏆 Won — 650 supporters Verified

Final supporters

E
Ermias W.
N
Nathaniel M.
B
Bezawit M.
S
Seife M.
B
belew
Z
Zewdu E.
A
Adbaru T.
M
Meseret K.
S
Someone
ተስፋዬ
+640 more
Started by Anonymous 14 years, 6 months ago

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ እና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ ነው፤ ለግሑሳን(ፍጹማን) ባሕታውያን መሸሸጊያ፣ ለስውራን ቅዱሳን መናኸርያ፣ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠሩ መነኮሳት፣ መነኮሳይያት እና መናንያን መጠጊያ፣ ለምእመናኑንም መማፀኛ እና ተስፋ ነው - የዋልድባ ገዳም፡፡

ቅዱሳን አበው እንደ ጽፍቀተ ሮማን የሰፈሩበት፣ እንደ ምንጭ የሚፈልቁበት ገዳሙ እመቤታችን ከልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ስደት ወቅት በኪደቱ እግር ከረገጧቸው መካናት አንዱ ነው፡፡ በወቅቱ ጌታችን

የወይራ ተክል ተክሎና አለምልሞ አርኣያ ስቅለቱን ገልጾበታል፤ ለቅዱሳኑ “እንደ ኢየሩሳሌም ትኹንላችሁ፤” ብሎ ቃል ኪዳን

በመስጠት እህል እንዳይዘራባት፣ ኀጢአት እንዳይሻገርባት፣ ከድንግል አፈሯ የተቀበረ እንዳይወቀስባት እንዳይከሰስባት

አዝዟል፡፡ በሰሜን ተራራዎች ግርጌ ዙሪያዋን በሰሜን አንሴሞ፣ በምሥራቅ ተከዜ፣ በምዕራብ ዘወረግ እና በደቡብ ዜዋ

በተባሉ አራት ወንዞች በተከበበችውና የኢትዮጵያ ገዳማት ሁሉ መመኪያ በተባለችው ገዳም ከሙዝ ተክል ከሚዘጋጀው

ቋርፍ እና ቅጠላ ቅጠል በቀር እህል አይበላባትም፡፡

በዚያ ቅዱሳን አበው፣ መነኮሳት እና መነኮሳይያት ረሀቡንና ጥሙን ታግሠው፣ የአገርን ቅርስና ሀብት ጠብቀው ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም እያለቀሱና እየጸለዩ፣ ዲማ በተባለው ፍልፍል ዛፍ በኣታቸው እያለፉ ኖረዋል፤ ቦታው ከፍተኛ የድኅነትና ሃይማኖት ሥፍራ ነውና ዛሬም ለአገር ሰላም፣ ፍቅርና ዕድገት ያልተቋረጠ ጸሎት እየተካሄደበት የሚገኝበት ቢሆንም ለ2000 ዓመታት በነገሥታቱ ሳይቀር ተጠብቆ የኖረውን ክብሩንና ሞጎሱን የሚፈታተን፣ ገዳማዊ ሕጉንና ሥርዐቱን የሚጋፋ፣ ማኅበረ መነኮሳቱንም ለከባድ ኀዘንና ጭንቀት የሚዳርግ አደጋ ተጋርጦበታል፡፡

የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበር፣ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም ማኅበር እና የዋልድባ

ዳልሽሓ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ማኅበር ምልአተ ጉባኤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ በጻፉት አምስት ገጽ

ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው፤ በዓዲ አርቃይ ወረዳ በኩል የዋልድባን ገዳም ውስጡን በፓርክነት ለመከላከል በቀለም የተቀለሙ ምልክቶች እየተተደረጉ ነው፡፡ በወልቃይት ወረዳ ልዩ ስሙ መዘጋ በተባለ የገዳሙ የእርሻ እና አዝመራ ቦታ ላይ

መንግሥት የዛሬማን ወንዝ ገድቦ የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በገዳሙ ክልል ዘልቆ

የሚያልፍ ጥርጊያ መንገድ ለመሥራት በግሬደር እና ሌሎችም ከባድ የሥራ መሣሪያዎች በሚካሄደው ቁፋሮ የቅዱሳን

አባቶች ዐፅም እየታረሰና እየፈለሰ መሆኑ የገዳሙን መነኮሳትና መናንያን ከፍተኛ ሐዘንና ጭንቀት ላይ ጥሏቸዋል፡፡

የማኅበረ መነኮሳቱ ደብዳቤ ጨምሮ እንደሚያብራራው የዛሬማ ወንዝ ግድብ ሲቆም በውኃ ሙላቱ ሳቢያ ከሚጠፉት የገዳሙ ወሳኝ ይዞታዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

1/ ልዩ ስሙ አባ ነፃ የተባለ የብዙ ቅዱሳን ዐፅም በክብር የፈለሰበትና የረገፈበት፣ ብዙ መነኮሳት እና መናንያን የሚቀመጡበት (የሕርመት/ተዐቅቦ ቦታ) የጻድቁ አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንና መቃብር እንዲሁምየሙዝ ቋርፍ በከፍተኛ ደረጃ የሚዘጋጅበት እጅግ ሰፊ የሆነ የአትክልት ሥፍራ፤ 2/ በመዘጋ የሚገኙት ሞፈር ቤቶች/በገዳሙ ውስጥ እህል ስለማይበላ የዓመት ቀለብ የሆነ ቋርፍ የሚዘጋጅበት የአትክልት ስፍራ/፤ 3/ በመዘጋ የገዳሙ መነኮሳት እህል የሚቀምሱበት ቤት፤<?xml:namespace prefix = o ns = "urn:schemas-microsoft-com:office:office" />

4/ ጥንታው

Updates

Reached 500 supporters

April 24, 2012

Reached 100 supporters

March 15, 2012

12 Comments

M
Meseret Kibret
11 years ago Featured

EGZIABEHER FERU GADAMACHANE YAMSARATAW Saw sayhone Earaso Madehane Alme Naw EHilewena gziabeher Feru Ya Gadame Guday Helwena Naw !!!! Qalteame Yateragalae !

M
Meseret Kibret
11 years ago Featured

EGZIABEHER FERU GADAMACHANE YAMSARATAW Saw sayhone Earaso Madehane Alme Naw EHilewena gziabeher Feru Ya Gadame Guday Helwena Naw !!!! Qalteame Yateragalae !

A
Anonymous
12 years ago Featured

e/r ethiopian yibark ehtoch wendemoch adera emenet ande nech ersuam orthodox tewahdo nech adera adera entebikat wesebhat le egzabher

A
Anonymous
12 years ago Featured

I am concerned about the persecuation of innocent monks and the destruction of Waldba.

T
Tewodros Weber
14 years ago Featured

Waldba is our spiritual heritage. Please stop the destruction of these holy places. God sees everything.

S
Selam Velez
14 years ago Featured

betam yikefetal waldba ye kidusane megebeya new adere le igziabher adere le tewahdo

S
Seife Miceal
7 years ago

I stand to protect th Gedam

B
belew
8 years ago

go on