Skip to main content
በአዲስ የውጭ ሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት ላይ ቅሬታና የመፍትሔ ጥያቄ ስለማቅ

በአዲስ የውጭ ሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት ላይ ቅሬታና የመፍትሔ ጥያቄ ስለማቅ

21 signatures 29 to reach 50
M
Muhammad a. signed 7 minutes ago
I
Ismael I. signed 1 hour ago
M
Mohammed C. signed 1 hour ago
M
Mekin S. signed 1 hour ago
F
fetiya h. signed 2 hours ago
H
Haider M. signed 2 hours ago
S
Seid A. signed 2 hours ago
A
ABDELLAH K. signed 2 hours ago
A
Abduselam A. signed 3 hours ago
AA
Started by Abduselam Awol 3 hours, 41 minutes ago
Decision Makers: Ministry of Labour and Skills

ለ፡ የፌዴራል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡ በአዲስ የውጭ ሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት ላይ ቅሬታና የመፍትሔ ጥያቄ ስለማቅረብ

ክቡራን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች፣

እንደሚታወቀው፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት አዲስ የውጭ ሥራ ስምሪት ኤጀንሲ ለማቋቋምና ሥራ ለመጀመር የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ከስምንት ወራት በፊት አሟልተን ማቅረባችን ይታወቃል። ሆኖም እስካሁን ድረስ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመጨረሻ ፈቃድ ማግኘት ባለመቻላችን ወደ ሥራ መግባት አልቻልንም።

ከዚህም በተጨማሪ፣ ጥቂት ኤጀንሲዎች ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ፈቃድ በማግኘት ሥራ መጀመራቸው እየታወቀ፣ እኛ ግን ሁሉንም አስፈላጊ መስፈርቶች አሟልተን ለረጅም ጊዜ ብንጠብቅም የመሥሪያ ቤቱን የመጨረሻ ውሳኔና ፈቃድ ማግኘት አልቻልንም።

ይህ ሁኔታ ኤጀንሲዎቻችንን በከፍተኛ የገንዘብና የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ ከመክተቱም በላይ፣ የተከራየና የተዘጋጀ ቢሮ፣ የሰው ኃይልና ሌሎች የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች ለረጅም ጊዜ ያለ ምንም ገቢ እንዲባክኑ አድርጓል። በተጨማሪም ፈቃዳችን በሲስተሙ ላይ ተንጠልጥሎ መቆየቱ የንግድ ሥራችንን ለመጀመር እንቅፋት ሆኖብናል።

በመሆኑም ከአዲሱ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመራር የምንጠብቀው፦

1. አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው ለረጅም ጊዜ የፈቃድ ማግኘት ሂደታቸው ተገትቶ የሚገኙ ኤጀንሲዎች ጉዳይ በአስቸኳይ እንዲታይ።
2. ለአንዳንድ ኤጀንሲዎች ፈቃድ ተሰጥቶ ሌሎች ተመሳሳይ መስፈርት ያሟሉ ኤጀንሲዎች የተገደቡበትን አሠራር በግልጽነትና በፍትሐዊነት እንዲገመገም።
3. የፈቃድ አሰጣጥ ሂደቱ በግልጽ፣ በተመሳሳይ መስፈርትና ያለ አድሎ እንዲፈጸም።
4. ለረጅም ጊዜ በሲስተሙ ላይ ተንጠልጥለው የሚገኙ የፈቃድ ጉዳዮች በአስቸኳይ ተፈትሸው ኤጀንሲዎቹ ሥራቸውን እንዲጀምሩ አስፈላጊው ውሳኔ እንዲሰጥ።

በመጨረሻም፣ እኛ ኤጀንሲዎች የመንግሥትን ሕግና ደንብ በማክበር፣ የተጠየቁትን መስፈርቶች አሟልተን ሥራ ለመጀመር ከፍተኛ ወጪና ጥረት አድርገናል። ስለሆነም የአዲሱ አመራር የፍትሐዊነት፣ የግልጽነትና የተቋማዊ ተጠያቂነት መርሆዎችን በመከተል ይህንን ችግር በአፋጣኝ እንዲፈታልንና ሥራችንን እንድንጀምር አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ከሰላምታ ጋር፣

4 Comments

S
Seid Assefa Verified
2 hr ago Featured

Since 2016 E.C., we have held a license and started the process under Version 1. However, the system suddenly stalled while we were paying office rent. We later continued under the new policy and have been waiting a long time for Level 5 approval. Meanwhile, we continue to pay office rent and employee salaries without generating any income. We kindly ask you to consider our situation and grant us the necessary approval as soon as possible so we can begin operations. Thank you for your consider

M
Muhammad abubeker Verified
5 min ago

to get the licence as soon as possible

M
Mekin Seid Verified
1 hr ago

I support fair recruitment and protection of domestic workers' rights.

A
ABDELLAH Kemal Verified
2 hr ago

ጋራንቲ አስገብተን ለረጅም ጊዜ ፍቃድ ሳንወስድ ከፍተኛ ኪሳራ ላይ ነው ያለነው

Help this petition grow

Share it with friends to help reach 50 signatures.

Your share link

Share directly