Skip to main content

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

319 Comments

ትዕግስት ሰጠኝ
10 years ago

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን በቤተ ክርስቲያናችን ዉስጥ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም የሚያገለግሉ መምህራኖች ነገር ግን የተሃድሶ መናፍቅ ትምህርት የሚያስተምሩ ላይ እርምጃ ይወሰድ በEBS ላይ የሚተላለፉ ታኦሎጎስ እና ቃለ አዋዲ ይዘጉልን

A
Anonymous
10 years ago

ይድረስ ለብፁአን አባቶቻችን በቤትክርስቲያናችን ውስጥ በኦርቶዶክስ ስም የሚያገለግሉ አገልጋዮች ነገርግን የተሀድሶ አስተምሮ እያስተማሩ ባሉ አገልጋዮች ላይ ዝምታው እስከመቼ ነው

B
Biruk Hailu
10 years ago

የአባቶቻችንን ውሳኔ እንጠብቃለን፡፡

H
Hayimanot tesfaye
10 years ago Featured

ቡራኪያችሁ ይድረሰን አባቶቻችን በ EBS የሚተላለፉ ቃለ አዋዲ እና ታኦሎጎስ የሚል ስርጭት እውነት ነው ይዘጋልን፡ ፡ በዱባይ የሚያገለግሉትንም እርምጃ ይወሰድልን ብዙ ነፍሳት እየጠፉ ነውና ሲኖዶሱ ከምንም ነገሮች በላይ በአሁኑ ስብሰባቸው የተሃድሶችን ጉዳይ በስፋት ቢመለከተው እንላለን ሰላም

E
Estifanos M.
10 years ago

zemetaw yebekal!!

T
Tenaye
10 years ago

I agree.

E
Esmelealem
10 years ago

May God bless our church!!!

T
TEMESGEN
10 years ago

እግዚአብሔር ሀገራችንን እና ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡፡

H
habtamu taddesse
10 years ago

በጎ መነሻ ነው ፤ነገር ግን አንዳንዶቹ ጥያቄወች ለአፈጻጸም የሚከብዱ በመሆናቸው የጥያቄወቹ አቅጣጫ እና ይዘት መለወጥ አለበት ብየ በግሌ አምናለሁ። ለምሳሌ ጥያቄ 3,4 እና አምስት ለአፈጻጸም የሚከብዱ ናቸው። ልብን የሚመርምር እግዚአብሄር ብቻ በመሆኑ የመንፈሳዊ ኮሌጁን የሚቀላቀሉ ሰወችን አፍራሽ ፍላጎት ማወቅ ይከብዳል።ስለዚህ በመንፈሳዊ ኮሌጁ ስም የማጭበርበር ስራ እንዳይሰራ ኮሌጁን ለማንኛዉም ሃይማኖት ላይ ጥናት ማድረግ ለሚሻ ሰው ክፍት ማድረግ።ነገር ግን ቤተክርስቲያኗ ለራሷ የምታሰለጥናቸዉን ሰወች እና የምትቀጥራቸዉን ሰወች በአጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ሰበካ ጉባኤ እና በማህበረሰቡ መልካም ስነምግባራቸው የተመሰከረላቸው እና ለቤተክርስቲያኗ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ እና እየሰጡ ያሉ ሊሆን ይገባል።እኔ ከዚህ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቅሁ ነኝ የሚል መናፍቅ ቢነሳ ፤ኮሌጁ ለማንኛዉም ሃይማኖትን ማጥናት ለሚፈልግ ሰው ስልጠና ስለሚሰጥ ማጭበርበር አይችሉም።ሁለተኛ ሃይማኖቷን ሌሎች እንዲያዉቁ በማድረግ ስለሆነ የማሸነፊያ መንገዱ ጥያቄው በተቃራኒ ቢሆን መልካም ነው። አራተኛው እና አምስተኛ ጥያቄወች አሁንም ለአፈጻጸም የሚከብዱ ናቸው፤ለምን ቢባል ሁለት ሲኖዶስ እንዳለ የሚያምን የኦርቶዶክስ አማኝ በዉጭ ሃገር በተለይ ብዙ ነው።መጀመሪያ ቀኖናውን ተከትሎ ሲኖዶስ እንደማትሰደድ ማስተማር እና በዉጭ ሃገር ስደተኛ ሲኖዶስ ነኝ የሚለው አካል የሚሰጣቸውን እዉቅናወች በመጠቀም ሃይማኖቷን በመከፋፋል እና ቀኖናወች እና ዶግማው በብዙ ቦታወች እየተጣሰ በመሆኑ የቤተክርስቲያኗ ተቀዳሚ ተግባር ዉጭ ካሉ አባቶች ጋር የእርቅ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል እና አቡነ መርቆሪወስ ከአገር ሲወጡ የነበረዉን እዉነታ ከዛም እሳቸዉን የተኩት ፓትሪያሪክ አቡነ ጳዉሎስ የተሾሙበት አግባብ እና አሁንም ያሉት አባት የተሾሙበትን አግባብ የሚያስረዳ እዉነትን ብቻ ያዘለ ነገር ማቅረብ ግድ ይላል።ከዚህ በኋላ ማህበረሰቡ ለእርቁ አለመሳካት ችግር በሚፈጥረው አካል ላይ ግፊት እንዲያደርግ ጥረት መደረግ አለበት።አሁን በትልቁ ተሃድሶወች እየተተቀሙበት ያለው ይህን የአባቶች ግጭት ነው።በተለይ ዉጭ ያሉ የዉጭ ሲኖዶስ አካል ነን የሚሉ አባቶች ለቀኖናው መፍረስ ቁብ እንደሌላቸው አስተዉያለሁ።ስለዚህ ከሁሉ በፊት እርቁ ይቅደም እላለሁ

A
Abebaw Abayneh
10 years ago

የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ የሚለውን የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል በሚገባ ማየት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ቤተክርቲያኗ የውስጥ ጠላት ሰለባ ከሆነች ብዙ አመታትን አስቆጠረች፡፡ በአሁኑ ሰዓት መናፍቃን እንደፈለጉት የቤተክርቲያንን ስርዓት የሚያፈርሱበትና ምዕመናንም እረኛ የሌላቸው በጎች የሆኑበት ዘመን ነው፡፡ ተሀዲሶ መፋፍቃን የሚደርጉትን የጥፋት ዘመቻ በአሁኑ ወቅት የማውቅ ከፍተኛ የሀይማኖት መሪ ያውም ደግሞ የሲኖዶስ አባል ይኖራል ብሎ መገመት ያስቸግራል፡፡አስቸኳይ መፍትሄ ካልተሰጠው በቀር መናፍቃን ከቤተክርስቲያን ለቅቃችሁ ውጡ የሚሉብን ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ለዚህም አበው ሲያውቅ የሞተን ሲሰማ ቅበረው ይላሉ፡፡ እስካሁን በእረኞች ችግር ተኩላ የበላቸውን ምዕመናን ብዛት ቤት ይቁጠረው፤ ለተበሉት በጎች ድግሞ እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል በተለይም ደግሞ ችግሩን ለመፍታት ቅርበት ያላቸው አባቶች በተሰጣቸው ኃላፊነት ልክ ጌታ መጠየቁ አይቀርም ፤ ጠብቁ ተብለዋልና፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶሱ ከላይ የተዘረዘሩትን ጥያቄዎችና ከክርስትና ስነምግባር አስተምሮ ውጭ የሚፈጸመውን የአዲስ አበባ ሀገረስብከትን የሙስና ችግር በአስቸኳይ ሊፈታ ይገባዋል እላለሁ፡፡

ተክለ እስጢፋኖስ
10 years ago

ቅድስት ቤተክርስቲያን ዛሬዛሬ እኛን የመሰሉ ነገርግን ከመናፍቃን ወገን የሆኑ በየደረጃው ለቤተክርስቲያኒቱ ትልቅ ፈተና ሆነዋት ይገኛሉ፤ በሥራቸውም ተለይተ ይታወቃሉ ሕዝቡን ማለያየ ማሳመጽ ብሎም ለህገ ቤተክርስቲይን ግድ እንዳይኖረው እያደፋፈሩት ነው ጠቅልለው ወደ መናፍቃን አዳራሽ እስኪወስዱት ሃይማኖቱን እንዲጠላ እና እንዲማረር እየተደረገ ያለበት ጊዜ ላይ ነን ለዚህም ዋነኛ ተባባሪ የሆኗቸው የኛው ነገር ግን የእኛ ያልሆኑ (የእኛን ማሊያ ለብሰው ለተቃራኒ የሚጫወቱ) ጳጳሳት ህዝባችንን ለጅብ እየሰጡብን ያለበት ዘመን ላይ ደርሰናል ስለዚክ ቅዱስ ሲኖዶስ እባላት ከሃዋርያት በአንብሮት እድ የተቀበላችሁትን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑት መልስ ስጡልን ቤተክርስቲያንን የመጠበቅ ግዴታችሁን አትርሱብን በረቱን ከነጠቦቶቹ መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታችሁም ነው

A
Anonymous
10 years ago

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

መስቀል ሀይል ነው
10 years ago

Comments

W
woubshet Tekalign
10 years ago

"LONG live orthodox tewahdo" ታኦሎጎስና ቃለ ኣዋዲ መዘጋት ኣለባቸው ፡፡እንዲሁም ክህነት ሳይኖራቸው የሚያስተምሩ መምህራን መታገድ አለባቸው፡፡

M
Melaku B.
10 years ago

Very nice looking to our Holy Synod.

T
tesfay gebru
10 years ago

Lets God be with us.

T
tesfay gebru
10 years ago

Lets God be with us.

K
Kahsay Hailu
10 years ago Featured

ታኦሎጎስና ቃለ ኣዋዲ መዘጋት ኣለባቸው። በቅዱስ ሲኖዶሱ ያሉ ህፀፅ ይሚታይባቸ ኣባቲች ሃገርና ትውልድ ሳያበላሹ ሊገሰፁና ሊወገዙ ይገባል። ባጠቃላይ ከቅድስት ቤተክርስትያኒቱ ዶግማ፥ ቀኖናና ትውዲት ብሎም ቅላፄ ውጪ የሆኑ ሁሉ በሽታቸው ይታወቃሉና ቅዱሳን ኣባቶች በፆምና በስባኤ መርምረው መፍትሄ እንዲያስቀምጡ እላለሁ።

G
geremew
10 years ago

(የይሁዳ መልእክት ምዕራፍ 1) ---------- 3፤ ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ። 4፤ ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።

W
Walelign Fikadu
10 years ago

የተጣለባችሁን አደራ ትወጡ ዘንድ በእግዚአብሔር ሥም እንጠይቃለን!!