Mezgebu Feleke 0

A Call for Peace and Reconcilation in EOTC

Show your support by signing this petition now
Mezgebu Feleke 0 Comments
0 people have signed. Add your voice!
0%

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

ተዋሕዶ ቤተ ክርስያን

ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

አዲስ አበባ                                                                       ነሐሴ ፲፮ ቀን ፪፻፻፬ ዓም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ ወኵሎ መራዕየ ዘሎቱ ሤመክሙ መንፈስ ቅዱስ ጳጳሳት ከመ ትርአዩ ቤተክርስቲያኑ ለክርስቶስ እንተ አጥረያ በደሙ

በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለእራሳችሁ ተጠንቀቁ

ግብ ሐዋርያት ፳፥፳፷

በውጭ አገር የምንኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስያን ካህናት፣ ዲያቆናትና መናን  ቤተክርስያን ዛሬ ስላለችበት ሁኔታ ለመነጋገር ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲመለከታቸው የምንፈልጋቸውን ሃሳቦች ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን፦

በቅድሚያ በብፁዕ ወቅዱስ / አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የዓለም የሰላም አምባሳደር ድንገተኛ ረፍት ምክንያት የተሰማንን ልባዊ ሃዘን እንገልጻለን። አምላካችን እግዚአብሔር የቅዱስነታቸውን ነፍስ ዐፀደ ሕይወት እንዲያሳርፍልን፣ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን እንዲቆጥርልን፤ መታሰቢያቸውንም ለበረከት እንዲያደርግልን የዘወትር ጸሎታችን ነው።

ዓን አባቶቻችን፦ በእውነተኛ ይታ ቀርበን ቤተክርስያናችን የተጓዘችበትን ያለፉትን ዓመታት ስንመለከት በእርግጥም እረኛዎችዋ የተከፋፈሉበት፣ በጎችዋ የተቅበዘበዙበት እርስ በእርሳችን ጥላቻና ጠብን ያተረፍንበት ከባድ የፈተና ዘመናት ነበሩ። ለዚህም ዋናው ምክንያት አንዲት ቤተክርስያን ውስጥ ያሉ አባቶች ለሁለት መከፈላቸውና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሌላ ሦስተኛ ገለልተኛ ወገን ደግሞ መፈጠሩ ነው። በአባቶች መለያየት ምክንያት የተፈጠረው ክፍተት መናፍቃን ጥቅመኞችና የፖለቲካ ሰዎች ለመለየት ሚያስቸግር መልክ በቤተክርስውስ እንዲሰገሰጉ አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል። ይህም ሁኔታ በአንዳንድ አገልጋዮች ዘንድ ቤተክርስትያን የተመሠረተችበትን መለኮታዊ ዓላማ እንዲስቱ የምእመናን ክርስትያናዊ ሕይወት እንዲደበዝዝ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሯል። ከዚህም በላይ ቅድስት ቤተክርስትያን በብሔራዊ ደረጃ የተፈጠሩ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የሚጠበቅባትን አዎንታዊ ሚና እንዳትጫወት ገድቧታል። በዘመናችን ይህ የታሪክ ስብራት በመፈጸሙና ተያይዞ ለተፈጠረው ፈርጀ ብዙ ቀው ሰለባ መሆናችን እጅግ እንድናዝንና እንድናፍር አድርጎናል። ይህ ለዘመናት የቆየና ስር የሰደደ ችግር ከእኛ ከልጆቻችሁ ይልቅ የሚበልጠውን ኃላፊነት የተሸከማችሁ ዓን አባቶቻችንን እጅግ የበለጠ እንደሚገዳችሁ መገመት አያቅተንም። አሁንም በከበራችሁበት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ተመርታችሁ፥ በብሩ አእምሮአችሁ መክራችሁ ለወደፊቷ ቤተክርስያን የሚበጀውን እንደምትሠሩ በሙሉ ልባችን ብናምንም ያለንበት ወቅት እጅግ ጥንቃቄ የሚያሻው ወሳኝ መሆኑ የሚከተሉትን ሦስት ነጥቦች ከግምት ውስ አስገብታችሁ እንድትመለከቱ በታላቅ አክብሮትና ትሕትና እንጠይቃለን።

አንደኛ፦ ቤተክርስያን ዛሬ ያለችበትንና የወደፊት አካሄዷን ስለማስተካከል በምትመክበትና በምትወስበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት መንግሥት በፍጹም እጁን እንዳያስገባ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ ሊከላከል ይገባል። ትላንት የተፈጸመ

Links


Share for Success

Comment

Signature

No signatures yet. Be the first one!