Ehiopian Students 0

A request

174 people have signed this petition. Add your name now!
Ehiopian Students 0 Comments
174 people have signed. Add your voice!
18%
Maxine K. signed just now
Adam B. signed just now

ቀን፡-ጥር 05 2009 ዓ.ም

ለ፡-ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስተር

ከ፡-ቻይና ሀገር በትምህርት ላይ የምንገኝ ተማሪዎች

ጉዳዩ፡-ችግሮቻችን እንዲፈቱልን ስለመጠየቅ

ክቡር ጠቅላይ ሚንስተር እኛ በቻይና ሀገር በትምህርት ለይ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ችነግሮቻችንን በጥልቀት ተወያይተን እርስዎ ይፈቱልናል ብለን በማመን በዝዝርዝር ከዚህ ሸኝ ደብዳቤ ጋር አባሪ አድርገን ልከንልዎታል፡፡

በደብዳቤያችን የተዘረዘሩትን ጥያቄዎቻችንን እልባት እንዲያገኙ ቢደረግ ና ችግሮች ቤፈቱልን ለሀገራቸን የሚኖረን በጎ አመለካከትና እምነት ከፍተኛ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ተመልሰንም ሀገራቸንን እንዲናገለግል ወኔ ይሰጠናል፡፡

ስለዚህም የኛ ችግር የሀገሪቱ ችግር እንደምሆን እርሶዋም ይገነዘባሉ ብለን እናምናልን፤ በመሆኑም ጊዜዎትን አጣበው ችግራችንን እንዲፈቱልን በትህትና እንጠይቃልን ፡፡

ከሰላምታ ጋር!

ግልባጭ

በቻይና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ጸ/ቤት

ቤጅንግ

ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ት/ሚኒስቴር

አዲስ አበባ

  • ጥያቄዎቻችን እንደሚከተለዉ በዝርዝር ተቀምጠዋል፤
  • ከዚህ ቀደም ትምህርት ላይ የነበሩ ተማሪዎች ከሚደረግላቸው ድጋፍ መካከል በውጭ ሀገር ሲማሩ በነበሩበት ጊዜ ይጠቀሙባቸው የነበሩትን የቤት ቁሳቁስ እና ተሸከርካሪ ያለ ቀረጥ እንዲያስገቡ ይፈቀድላቸው ነበር:: ነገር ግን ይኽ ድጋፍ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከተወሰኑ መገልገያ ዕቃዎች ውጪ ማስገባት እንዳይቻል ተደርጓል፡፡ ይኽም፡- ደግሞ ተማሪዎች በውጭ ሀገር ስንማር በቆየንባቸው ጊዜ ያሰባሰብናቸው ንብረቶች ወደ ሀገራችን ማስገባት ባለመቻላችን ምክንያት ብቻ የሚከተሉትን አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮብናል፡-
  • በቆይታው በኖርንበት ሀገር የኑሮ ደረጃ መሠረት የገዛናቸውን መገልገያ ዕቃዎች ይዘን ወደ ሀገሩ መግባት ባለመቻሉ ዕድሉን ካገኘን በከፍተኛ ቅናሽ በመሸጥ ካልሆነም ትቶ ለመምጣት ስለምንገደድ ሀገራችን ከተመለሰን በኋላ ድጋሚ ወደ መቋቋም የምንገባበት ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ ይህ ደግሞ በሀገር ውስጥ ካለው የኑሮ ሁኔታ አንጻር ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር ሆኗል፡፡ወደ ሀገራችን ከተመለስንም በኋላ አቅም ኖሮን መግዛትብንችል እንኳን ሀገሪቱ እነዚህን ዕቃዎች በውጭ ምንዛሬ እንድታስገባ ስለሚያስገድዳት ሌላ ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡
  • በሁለተኛ ደረጃ፡- ልክ እንደኛው ሁሉ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በኢኮኖሚ ከሀገራችን የማይበልጡ ሀገራትን ጨምሮ የሚመጡ ተማሪዎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ከሚደረግላቸው ድጋፍ አኳያ ሲታይ ተሸከርካሪና ማንኛውንም ዕቃ ከቀረጥ ነጻ በሆነ መልኩ ወደ ሀገራቸው ማስገባት እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ለእኛ ሀገር ተማሪዎች የተከለከለ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ ሥነ-ልቦናዊ ተፅዕኖ አሳድሮብናል፤ በዜግነታችንም የበታችነት ስሜት እንዲኖረን አድረጓል፡፡ በተጨማሪም ተምረን ሀገራችን ስንመለስ የሚኖረን የኑሮ ሁኔታ ዝቅተኛ በመሆኑ በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚኖረን ቅቡልነት አነስተኛ እንዲሆን አድርጎታል ፣ ከዚህ ጋር በተያይዘ የተፈጠረብን ሥነ-ልቦናዊ ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ ሀገራችንን ለማገልገል የሚኖረንን ተነሳሽነት ደካማ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ እንዲሁም በዛው የመቅረቱ አዝማሚያ እየጨመረ መጥቷል ፡፡
  1. በቻይና ሀገር የምንማር ኢትዮጵያውያን ትምህርታችንን አጠናቀን ወደ ሀገራችን ስንመለስ የትምህርት ማስረጃችን የአቻ ግመታ እነድሚደረግ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የአቻው ግመታውን ለማድረግ ቻይና ያለውን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ማረጋገጫ ማኅተም ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን ኢምባሲያችን በአንድ ነጠላ ሰነድ ወደ 392 የቻይና ገንዘብ፤ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ በሰነድ 476 የቻና ዩዋን የሚያስከፍል ሲሆን በአጠቃላይ በነጠላ ሰነድ 868 የቻና ዩዋን መክፈል ይጠበቅብናል፡፡ ያም ማለት አንድ ተማሪ ቢያንስ ሦስት ሰነዶችን ማረጋገጥ ስለሚጠበቅብት በትንሹ 2604 የቻይና ዩዋን መክፍል ይጠበቅበታል ማለት ነው፡፡ ይኽ ደግሞ እየተማረ ቤተሰቦቹን ለሚረዳ፣ በግማሽ ስኮላርሺፕ እና በብዙ ችግር እየተማሩ ላሉ ተማሪዎች የሚፈጥረው ኢኮኖሚያዊ ጫና በጣም ከፍተኛ እና አስጨናቂ ሆኖብናል፡፡
  2. ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ተለያዩ ሀገራት ለትምህርት የሚልካቸውን ተማሪዎች በሙሉ ወደ ሀገራቸው ተምልሰው እንዲገለግሉ ውል በማስገባት የኪስ ገንዘብ እየከፈላቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ጅምሩ መልካም ሆኖ ሳለ ነገር ግን እየተማርን ካለንበት ሀገር የኑሮ ደረጃ እና ራሳችንንም ከመደጎም አኳያ ሲታይ እግጅ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ በኢኮኖሚ ከሀገራችን የማይሻሉ የአፍሪካ ሀገራት ድጎማ አንጻር እንኳ ሲታይ ለንጽጽር የሚቀርብ አይደለም፡፡
  3. በገል ጠረታችን ነጻ የትምህርት ዕድል ፈልገን የተለያየ ደረጃ ያለው ስኮላርሺ አግኘተን ለትምህርት ወደ ቻይና ሀገር የመጣን ተማሪዎች በትምህርት ላይ እያለን የሚከፈለን ክፍያ ዝቅተኛ ስለሆነ እየተቸገርን እንገኛለን፡፡
  4. ለእረፍትም ሆነ ትምህርታችንን አጠናቀን ስንመለስ በአብዛኛው የምንጠቀመው የሀገራችንን አየር መንገድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ተማሪዎች እንደመሆናችን መጠን የእረፍት ጊዜያትን እና የትምህርት ማጠናቀቂያ ጊዜያትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ልክ ሕንድ ሀገር ለሚማሩ ተማሪዎች አንደሚደረግላቸው ዓይነት የዋጋ ቅናሽ በአየር መንገዳችን በኩል ባለመደረጉ ምክኒያት የእድሉ ተጠቃሚ ልንሆን አልቻልንም፡፡
  5. እንደሚታወቀው ከመንግስታ ጋር ውል ገብተን ለትምህርት ስንመጣ የነበርንበት መሥሪያ ቤት ተቀጣሪነታችን እንደተጠበቀ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በመንግሥት በኩል ለተቀጣሪው የሚደረጉ ጥቅማጥቅሞች ሁሉ በትምህርት ላይ ላለነውም እንደሚመለከተን ታሳቢ ሆኖ ሲተገበርም ቆይቷል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ አገር ቤት የሚደረጉ ጥቅማ ጥቅሞች ላይ ግን በአካል ባለመኖራችን ምክንያት እንድናጣ የሚሆንብት ሁኔታ አለ፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ መንግሥት ለመምህራን ቃል የገባው የመኖሪያ ቤትን ወይም ለመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታን በተመለከተ በአንዳንድ ተቋማት ያለ አግባብ መንግሥት ያመመቻቸልንን ዕድል ተጠቃሚ እንዳንሆን ተደረጓል፡፡
  6. በሌላ በኩል ውጭ ሀገር የምንማር ተማሪዎች በስራችን የሚተዳደሩ ቤተሰቦች ያለን በመሆኑ ከዚህ በፊት በሙሉ ደሞዝ ሲተዳደር የነበረው ቤተሰብ ወደ ግማሽ ደሞዝ ዝቅ ሲል ካለው ኑሮ ውድነት አንጻር በቂ ባለመሆኑ ምክንያት ቤተሰቦቻችን ከፍተኛ የሆነ ችግር ላይ ወድቀዋል፡፡ በመሆኑም ልጆቻችንን ማስተማር ፤ የቤት ኪረይና መቀለብ ባለመቻላችን በስነልቦና ተጎድተናል፡፡

ማጠቃለያ ፡-

  • በውጭ ሀገር ትምህርት ላይ እያለን ስንጠቀምበቸው የቆየንባቸውን የቤት መኪና ና ማንኛውንም እቃ ከቀረጥ ነጻ እንድናስገባ እንዲፈቀድልን፡፡
  • ግሙሩክ አካባቢ የሚሰሩ አንዳንድ ሰራተኞች የተፈቀደልንን እቃ ይዘን ስንገባ እነኳ የሚያደርሱብን እንግልትና መጉላላት እንዲቆም እንዲደረግልን፡፡
  • በኢትዮጵያ እምባሲና ቁንስላዎች የሚጠይቁን የተጋነነ የትምህርት ማስረጃ አቻ ግምታ ክፍያ እንዲቀር ልን፡፡
  • በትምህርት ሚኒስተር በኩል የሚደረግልን የኪስ ገንዘብ ድጋፍ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ የሌሎች ሀገሮችን ተሞክሮ በመመልከት ማሻሻያ እነዲደረግልን፡፡
  • በግል ጥረታችን ነጻ የትምህርት ዕድል ያገኘን ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች እኩል ማንኛውም ድጋፍ እንዲደረግልን፡፡
  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ህንድ አገር ላሉ ተማሪዎች እንደሚደረገው የአየር ትኬት ቅናሽ ተጠቃሚ እንድንሆን፡፡
  • አገር ውስጥ ላሉ መምህራን መንግስት ቃል በገባው መሰረት የመኖሪያ ቤት ወይም የመስሪያ ቦታ እንዲሰጠን፡፡
  • ውጭ ሀገር ለምንማር ተማሪዎችን እየተከፈልን ያለው ግማሽ ደመወዝ ካለው ኑሮ ውድነት አንጻር በቂ ባለመሆኑ ምክንያት ቤተሰቦቻችን ችግር ላይ ወድቀው ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ሙሉ ደሞዝ እንዲከፈልን እንጠይቃልን፡፡

ስለዚህ የተከበሩ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠ/ሚኒስተር ከዚህ በላይ አብራርተን የገለጽናቸውን ጉዳዮች ካለንበት ችግር አኳያ በጥልቀት ና በባለቤትነት ስሜት እንዲያዩልንና መፍትሄ እንድሰጡን በቻይና ሀገር የምንገኝ የኢትዮጵያ ተማሪዎች በታላቅ አክበሮት እንጠይቃልን፡፡

Share for Success

Comment

174

Signatures