Petition for Emergency ECAA Meeting August 24, 2025 2:00 PM
Date of Meeting: Sunday, August 24, 2025
Time: 2:00 PM
Location: 5616 Memorial Drive, Stone Mountain, GA 30083
ይድረስ ለኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አባላት በአትላንታ
በመተዳደርያ ደንባችን መሰረት በየሁለት አመት አዲስ የስራ አመራር፣ የቦርድ አባላትና የቁጥጥር ኮሚቴ
በጠቅላላ ጉባኤ እንደሚመረጥ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ጁነ . ቀን 2024 አመተ ምህረት በተደረገው
ጠቅላላ ጉባኤ 4 የ ቦርድ አባላት፣ 9 የአመራር ኮሚቴ አባላትና 3 የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት መመረጣቸው
ይታወቃል። በተጨማሪም በድርጅታችን መተዳደርያ ደንብ መሰረት የሃይማኖት ተቋማና የተለያዩ
የበጎአድራጎትና የሲቪክ ማህበራት የየድርጅታቸውን የቦርድ አባላት እንዲወክሉ ተደርጓል።
በዚህ መሰረት በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡትና በተለያየ ድርጅቶች የተወከሉት የቦርድ አባላት በድምሩ 22
ነበሩ።
የተከበራችሁ የ ኮሙኒቲ አባላት
እነዚህ ከላይ ከተዘረዘሩት የቦርድ አባላት ጥቂቶቹ ከዳይሬክተሩና ከሌሎች የቦርድ አባላት ጋር በፈጠሩት
አለመግባባትና ውዝግብ ምክንያት የኮሙኒቲው ስራ ተደናቅፏል። የቦርዱ ሊቀ መንበር፣ የቦርድ ምክትል
ሊቀ መንበርና፣ የቦርድ ጸሃፊ በደረሰባቸው ከባድ ዘለፋና አሳፋሪ ዘረኝነት ክሃላፊነታቸው እንዲለቁ
ተገደዋል።
የ2017 የአዲስ ዓመት በአል ከተከበረ በኋል ምንም አይነት ሥራ ለመሥራት ማለመቻሉ ፌብሩዋሪ 2፣
2025 ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ስለችግሩ መግለጫ ካገኘ በኋል መፍትሄ ይሆናል ብሎ ያሰበውን
የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፎአል።
1ኛ፣ አዲስ የመተዳደሪያ ደንብ አርቃቂ ኮሚቴ ተመርጦ አወዛጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን እንዲመረምርና ተለዋጭ
ረቀቅ ደንብ ለጠቅላላ ጉባኤው አቅርበው እንዲያጸድቁ፣
2፣ የተስተካከለው ደንብ በሚጸድቅበት ቀን አስመራጭ ኮሚቴ እንዲመረጥና አሁን በስራ ላይ ያሉት
አመራሮች ወርደው በአዲስ ተመራጮች እንዲተኩ፣
3፣ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ክአስቸኳይ ሥራዎች ውጪ በማንኛውም የኮሙኒቲው
አካላት ምንም ሥራ እንዳይሠራ ጠቅላላ ጉባኤው ወስኖ ጉባኤው ተበትኗል።
እነዚህ የጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔዎች ተግባር ላይ ሳይውሉ፣ በህዝብ የተመረጠውን የአስተዳደር ዲሬክተር
ከስራ አግደው፣ በለውጡ ሌላ ዲሬክተር ሾመው፣ በጆርጅያ መንግሥት ውስጥ ያለውን ምዝገባ ቀይረው፣
የባንክ ሂሳቡን ተቆጣጥረዋል። ይህንን ያደረጉት እኛን አብዛኛውን የቦርድ አባላት አግልለው ጥቂት የቦርድ
አባላት በፈጠሩት የወራሪ ኃይል አማካኝነት መሆኑ እንዲታወቅልን እንጠይቃለን።
ይህ ሁሉ የሀገወጥ ድርጊት አልበቃቸው ብሎ የማህበራችንን ስም በመጠቀም ዲሬክተሩ በአስቸኳይ ከስራ
እንዲወገድ የፍርድ ቤት ክስ መስርተዋል። ይህ ህገወጥ ሂደት ያሳሰባቸው አንድ አንድ ድርጅቶች ለቦርድ
አባልነት የወከሏቸውንና ዲሬክተሩ እንዲነሳ ድምጽ የሰጡት የቦርድ አባላት ድምጻቸው እነሱን የማይውክል
መሆኑን አስታውቀው ውክልናቸውን ማንሳታቸውን በደብዳቤ ለኮሙኒቲው አሳውቀዋል። በዚህም
መሰረት የተስፋ ድርጅትና የማርያም ቤተክርስትያንን ወክልው የመጡት ሁለት ግለሰቦች ከያዙአቸው
የቦርድ አባልነት ተነስተዋል። በተጽኖ ምክንያት ከሃላፊነት የለቀቁትና ከውክልናቸው በድርጅታቸው
የተውገዱት 5 አባላት በመቀነሳቸው በአሁኑ ወቅት የቦርድ አባላት ቁጥር ከ22 ወደ 17 ወርዷል
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ኮሙኒት አባላት በአትላንታ
እኛ ከዚህ በታች ስማችን የተዘረዘረው 10 የቦርድ አባላት በህገወጥ መንገድ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ
በመሯሯጥ ላይ ያሉትን ግለሰቦች ድርጊት አጥብቀን እንቃወማለን። የድርጅታችንን ህልውና ወደአስጊ ደረጃ
አውርደውታል። ሰለዚህም አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራና ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጠው በጠየቅነው
መሰረት የፊታችን እሁድ August 24, 2025 8:00 pm በኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አዳራሽ ስብሰባው እንዲደረግ
ጥሪው በዲረክትሩ በኩል ተላልፏል። ይህ ጠቅላላ ጉባኤ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ በድርጅታችን ላይ
እየአንዣበበ የለዉን አደጋ በቅርብ ተገንዝባችሁ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በተጠራዉ ጉባኤ ላይ
እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።
የቦርድ አባል
የወከላቸው አካል
1 ደበበ ይርጉ
2 ሶስና በቀለ
3 ታከለ ደበሌ
4 ዲንቃ በቀለ
5 ሳምሶን ሃይለየሱስ
6 አስቴር ሃብተስላሴ
7 የአዛብነሽ ወርቁ
8 ደረጀ መኮንን
9 ጥላሁን መገርሳ
10 ምትኩ ተሾ
We therefore request and support this Emergency Meeting to be held on Sunday, August 24, 2025, at 2:00 PM at the ECAA office, 5616 Memorial Drive, Stone Mountain, GA 30083.
Enter your details on the next page
Comment
See More 0