ለቅዱስ ሲኖዶስ አንድነት የበኩላችንን እንወጣ
11
people have signed this petition. Add your name now!
11
people have signed. Add your voice!
2%
Maxine K. signed
just now
Adam B. signed
just now
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አስተዳደሯ ለሁለት ተከፍሏል። በዚሁም የተነሳ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ፓትርያሪክ አቡነ መርቆርዮስ በስደት እንደሚኖሩ ይታወቃል።
በቅርቡ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ብፁዓን አባቶች የተፈጠረውን የሥርዓት መጣስ ለመፍታት እና የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት ለመመለስ ከሁለቱም በኩል የሚነጋገሩት አባቶች ተመርጠው ሥራ ለመጀመር እየተዘጋጁ ነው። ለዚህ የተቀደሰ ተግባር የምዕመናን ሁለንተናዊ ድጋፍ ወሳኝ ነው።
ስለሆነም ከእዚህ በታች ያለውን የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰቢያ (ፔቲሽን) እንዲፈርሙ እንጠይቃለን።
የተሰበሰበው ፔቲሽን ለሁሉም ብፁዓን አባቶች እንዲታረቁ ከሚጠይቅ የተማፅኖ ደብዳቤ ጋር እንዲደርስ ይደረጋል።
የእርስዎ በቶሎ መፈረም አስፈላጊ ነውና አሁኑኑ ይፈርሙ ::
Comment