ለቅዱስ ሲኖዶስ አንድነት የበኩላችንን እንወጣ

Getachew Bekele
Getachew Bekele 251 Comments
438 SignaturesGoal: 1,000

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አስተዳደሯ ለሁለት ተከፍሏል። በዚሁም የተነሳ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ፓትርያሪክ አቡነ መርቆርዮስ በስደት እንደሚኖሩ ይታወቃል።

በቅርቡ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ብፁዓን አባቶች የተፈጠረውን የሥርዓት መጣስ ለመፍታት እና የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት ለመመለስ ከሁለቱም በኩል የሚነጋገሩ አባቶች ተመርጠው ለእርቀ ሰላም እየተዘጋጁ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህ የተቀደሰ ተግባር የምዕመናን ሁለንተናዊ ድጋፍ ወሳኝ ነው።ለእዚህም ይረዳ ዘንድ ይህ የፊርማ ማሰባሰብያ (ፔቲሽን) ተዘጋጅቷል።

የእዚህ የፊርማ ማሰባሰብ ዓላማ ምዕመናን በአባቶች መለያየት ምክንያት መንፈሳዊ ህይወታቸውን እና ማኅበራዊ አንድነታቸውን በእጅጉ ስለተጎዳ የእርቁን ጉዳይ በጣም ቅድምያ እንደሚሰጡት እና በአንክሮ እንደሚከታተሉት እንዲሁም ከእርቀ ሰላሙ ውጭ ሌላ ምንም አይነት መፍትሄ እንደሌለ ለብፁዓን አባቶች በልጅነት አንደበት ለመማፀን ነው።

ስለሆነም ከእዚህ በታች ያለውን የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰቢያ እንዲፈርሙ እንጠይቃለን።

የተሰበሰበው ፊርማ ለሁሉም ብፁዓን አባቶች እንዲታረቁ ከሚጠይቅ የተማፅኖ ደብዳቤ ጋር እርቀ ሰላሙ ከመጀመሩ በፊት ለብፁዓን አባቶች ይላካል።

የእርስዎ በቶሎ መፈረም አስፈላጊ ነውና አሁኑኑ ይፈርሙ::

ለሚያውቁት ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይህንን የፊርማ ማሰባሰብያ ሊንክ እንዲልኩላቸው በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ስለትብብርዎ እናመሰግናለን።

251

Comments

See More
438

Signatures