We Asked for Our Homes Not Imprison Ermyas Amelga
ለክቡር አቶ መኩሪያ ሀይሌ - የፌደራል ቤቶች ልማት ሚ/ር
ለክቡር አቶ ጌታቸው አምባየ - የፌደራል ፍትህ ሚ/ር
ለክቡር አቶ ያቆብ ያላ - የፌደራል ንግድ ሚ/ር
ለክቡር አቶ አሰፋ - የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽነር
መንግስት በአክሰስ ሪል ስቴት አ/ማ የተፈጠረውን ችግር በመፍታት ቤት ገዢዎች ቤት የሚያገኙበትነ ሁኔታ ለመፍጠር የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማዋቀር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ እኛም ይህ መንግስት የሚያድገውን እንቅስቃሴ በመደገፍ የኩባንያው ችግር ተፈትቶ ቤቶችን የምንረከብበት ጊዜ በተስፋ እየተጠባበቅን እንገኛለን፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ አብይ ኮሚቴው ጥር 02 ቀን 2008ዓ.ም በተጠራው የቤት ገዢዎች ስብሰባ ላይ በኩባንያው የተፈጠረውን ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የራሳቸውን ጥቅም የሚያሳድዱ የተወሰኑ ኃይሎች ተደራጅተው በመግባት የተለያዩ ወረቀቶችን ተጻጽፈው በመለዋወጥ ሁካታና ግርግር መበፍጠር የስብሰባ አካሄዱን በመቀየረ መፍትሄ በማያመጣ መንገድ ስብስበው እንዲቋጭ አድርገዋል፡፡
ስለሆነም እኛ ከዚህ በታች ስማችንና ፊርማችን የተገለጸው ቤት ገዥዎች ጥር 02 ቀን 2008ዓ.ም በተደረገው ስብሰባ ላይ የተንጸባረቀው ሀሳብ እና የተደረሰበት ድምዳሜ እኛን የማይወክል፣የቤት ገዥዎችን ችግር የማይፈታ በመሆኑ እና በአሁኑ ሰዓትም ቤት ለሚፈልጉት ቤት እና ገንዘብ ለሚፈልጉት ደግሞ ገንዘብ መስጠት አቅም ያለው የቻይና ኩባንያ የተገኘ መሆኑ ስለተረዳን የአቶ ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ መታሰር ከጥቀም ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ ከእስር ወጥተው ለችግሩ የመፍትሔው አካል እንሆኑልን እንጠይቃለን፡፡
Comment