ቅዱስ ሲኖዶስ ጥቅምት 12 ቀን ለሚከናወነው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ብጹአን አባቶች ምላሽ እንዲሰጡበት በዝርዝር የተጠየቁትን ጥያቄዎች እደግፋለሁ፡፡

Tewodros Birhanu
Tewodros Birhanu 692 Comments
1,255 Signatures Goal: 20,000በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ
ወጣቶች እና ጎልማሶች መንፈሳዊያን ማኅበራት ኅብረት

ለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጥንት ዘመን ታገኝ የነበረውን ርስት ጉልት ተነጥቃ በምዕመናን ምጽዋት፤ ችሮታና የስለት ብር መተዳደር ከጀመረች ከሦስት አሠርት ዓመታት በላይ አስቆጥራለች፡፡ በተለይም የኢኮኖሚ የበላይነት ከፍተኛ ተገግዳሮት በሚፈጥርበት አሁን ባለንበት ዘመን ደግሞ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ከየትኛውም መንግሥታዊ ከሆነም ሆነ መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ድጋፍ ሳይደረግላት ዋና የበጀትና የገቢ ምንጯ የምዕመናን ምጽዋትና ችሮታ በመሆኑ ከላይ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ ታች መዋቅር ድረስ ያሉ ሠራተኞች ደመወዝ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ፈተናዎችን እያለፈች በልማት ጎዳና ላይ ትገኛለች፡፡

ለዚህም የየሀገረ ስብከቱ፤ የየገዳማቱና የየአድባራቱ እንዲሁም የመንፈሳዊ ኮሌጆች ሕንጻዎች ሳይቀር ከምዕመናን በተሰበሰበ የሙዳየ ምጽዋት ውጤት የታነጹ እንጂ የትኛውም የውጭ ድርጅት ጣልቃ ገብነት ያለበት የገንዘብ ፈሰስ አለመኖሩ ምዕመናን ለቤተ ክርስቲያናችን ዋነኛ የገቢ ምንጭ መሆናችንን ያሳያል ፡፡

ይሁንና ይህ የምዕመናን አስተዋጽኦ ከፍተኛ በሆነበት ሁኔታ ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በመንበረ ፓትርያርክ ስም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስም፤ እና በሀገረ ስብከት ስም የሚወጡ ቀላጤ መመርያዎች ምዕመናኑን ባለማገናዘባቸው የምዕመናንን ማንነትን፤ የቤተ ክርስቲያናችንን መዋቅርና የሃይማኖታችንን ቀጥተኝነት እያናጋው ስለመሆኑ የሚከተሉት ሦስት ነጥቦች ያስረዳሉ ፡

 • ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመዋቅር አሠራር በሚል ሰበብ ሰባክያነ ወንጌልን በተመለከተ በሀገረ ስብከት ስም የወጣው መመርያ በተለይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሰባክያነ ወንጌል ላይ የጣለው እገዳ ሲመረመር መታገድ ያለባቸው ግለሰቦች ካሉ ሀገረ ስብከቱ ስማቸውን ጠቅሶ ማገድ ሲገባው በጅምላ በመዋቅር ውስጥ የሌሉ አገልጋዮች እንዳይሰብኩ በሚል ያስተላለፈው ቀላጤ የእገዳ መመርያ ምዕመናንን በመናፍቃን ለማስወሰድ ሆን ተብሎ የተመቻቸ ስለመሆኑ የሀገረ ስብከቱ የእገዳ ሂደትና አዲሱ የሰባክያን የቅጥር አካሄድ ተመጋጋቢነት ያስረዳል፡፡
 • ከውጉዙ አሰግድ ሳህሉ ጋር ተሰይመው በተወገዘው ቃለ አዋዲ በተሰኘው ጣብያ መግለጫ ሲሰጡ የታዩት አንዳንዶቹ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመራቂዎች በመሆናቸው አሰግድ ሳህሉም የዚሁ ት/ት ቤት ተመራቂ መሆኑን በማስረጃ ለመግለጽ በመሞከሩ እርሱንና ግብረአበሮቹ መናፍቃን ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ እንዴት ሊያፈራቸው እንደቻለ እየታወቀ በኮሌጁ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለው የተበላሸ አሠራር በዝምታ መታለፉ እጅግ ያሳዝናል፡፡
 • በእኛ በምዕመናን የምጽዋት፤ የችሮታና የስዕለት ብር አማካኝነት በሚልዮን ብሮች በጀት የተያዘለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቴሌቪዥን ስርጭት በመዋቅሩ ስር ያለውን ማኅበረ ቅዱሳንን ሰዓት ሰጥቶ መርሐ ግብሩን እንዲያስተላልፍ አለመፍቀዱ ሲታይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የቴሌቭዥን ሥርጭት የማን ተዋካይ ሆኖ ሊሠራ እንዳሰበ ግልጽ አይደለም፡

ስለሆነም ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ የሾማችሁ አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ጳጳሳት በቅዱስ ፓትርያርኩ ሰብሳቢነት ጥቅምት 12 ቀን በምትጀምሩት ዓመታዊ የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ በአጀንዳነት እንድትወያዩበትና ውሳኔ እንድትሰጡበት እኛ ምዕመናን ልጆቻችሁ ይህንን ማመልከቻችንን ስናቀርብ የሚከተሉትን መፍትሔ ጠቋሚ ሐሳቦችን በመጠየቅ ነው፡፡

 • ስማቸው በአባሪ የተያያዘው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አማካኝነት የተቀጠሩትና ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በኃላፊነት የተሰየሙ ግለሰቦች የሚያስተላልፉት ትምህርት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ባለመሆኑ እንዲታገዱልን፤ ማጣርያ የሚያስፈልገቸውም ከሆነ እየሰሩ ሳይሆን ታግደው ማጣርያ እንዲደረግባቸው፤ ከእገዳው በኋላም ለሚደረገው የማጣራት ሂደት በእያንዳንዱ ላይ አስፈላጊውን መረጃ እንዲታይልንና የሰው ምስክርም እንዲሰማልን ስንል አበክረን እንጠይቃለን፡፡
 • በአንጻሩም አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የጣለውን የጅምላ እገዳ እንዲያነሳና ማስተማር የሌለባቸው ግለሰቦች ካሉ ስማቸው ተጠቅሶ እንዲታገዱ በቀሩት ስማቸው ባልተጠቀሰው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መምህራነ ወንጌል በሆኑት ታማኝ የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ መደበኛ ቅጥረኛ አይደላችሁም የሚል ሰበብ ተነሥቶ እንዲያስተምሩ ይደረግ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ እንዲሰጥበት ስንል በትህትናና በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
 • በምዕመናን ምጽዋትና ቤተ ክርስቲያናችን ባከበተችው ገንዘብ የጎለበተው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጃችን እንደነ አሰግድ ሳሕሉ ዓይነት መናፍቃንን በማፍራቱ ኮሌጁ እየሄደበት ያለበትን ሁኔታ እንዲጠናና የኮሌጁ ሥርዐተ ትምህርት፤ ከተማሪዎች ምልመላና የትምህርት ማስረጃቸው እውነተኛነቱ ሳይቀር እንዲመረመር እየጠየቅን ከምረቃ በኋላ ያሉ የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት የቤተ ክርስቲያናችንን የትምህርት ማስረጃ ከያዙ በኋላ የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ ቀኖና ትውፊት በማፋለስ የምንፍቅናን ትምህርት እያስተማሩ ያሉት ዉጉዛን ወይም ውጹኣን ማስረጃ አለን ከቤተ ክርስቲያን ተገፍተን ነው የወጣነው ለማለት የሚያሳዩትን የኮሌጃችንን የዲግሪ ወይም የዲፕሎማ ማስረጃ እንዲመልሱና አልባሳቱን እንዲያወልቁ የሚደረግበት ውሳኔ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን፡፡
 • እስከምናውቀው ድረስ ማኅበረ ቅዱሳን በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ተቋም ሥር ያለ የቤተ ክርስቲያናችን ሕጋዊ አካል መሆኑ ግልጽ ነው ፡፡ ስለሆነም የማኅበረ ቅዱሳን

ዓላማ እቅዱና ራእዩ በቅዱስ ሲኖዶስ እስከጸደቀ ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተቋም ስር ባለው የቴሌቭዥን ጣብያ የማይስተናገድበት ምክንያት ግልጽ አይደለም፡፡ ከዚህም አኳያ ማኅበረ ቅዱሳን የስርጭት ሰዓት ስላልተሰጠው የራሱ የሆነ የቴሌቭዥን ስርጭትም በሌላ በአማራጭ በመክፈት የሚያስተላልፈውን ትምህርት መከታተል ስንጀምር ከጠቅላይ ቤተ ክህነት በወጣ ደብዳቤ ስም ለማሳገድ መሞከሩ የመርሐ ግብሩ ተደራሽ የሆንን ምዕመናንን የሚያሳዝን ስለሆነ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስም የወጣውን ደብዳቤ እንቃወማለን ፡፤ ይልቁንም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚሠሩትን ስውር መንገዶችንና የተድበሰበሱትን አሻጥሮችን ግልጽ በማድረግ በዋናነት ማኅበረ ቅዱሳን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን የቴሌቭዥን ጣብያ መርሐ ግብር እንዲሰጠው ወይም እየሄደበት ያለው የአጣብቂኝ አማራጭ የቴሌቭዥን ስርጭት እንዲፈቀድለት ስንል የቅዱስ ሲኖዶስ ጽኑ ውሳኔን እንጠብቃለን፡፡

ባጠቃላይ ቤተ ክርስቲያናችን ከጥንት ጀምሮ ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን የሚቃጣባትን ፈተናዎችን እየተቋቋመች በአበው ሊቃነ ጳጳሳት ጥበቃና ተጋድሎ ድል የምታደርግ መሆኗ ይታወቃል፡፡ የዚህች ቤተ ክርስቲያን እንደራሴ የሆናችሁ አበው ሊቃነ ጳጳሳትም ከላይ ነጥብ በነጥብ የተዘረዘሩት ጥያቄዎች መልስ ትሰጡናላችሁ ብለን ተስፋ ስለምናደርግ ይህንን አቤቱታ ስናቀርብ በደስታ ነው፡፡ ነገር ግን ጥያቄያችን መልስ እስኪያገኝ ድረስ ምዕመናን ተሰብስበን በአካል ሲኖዶሱን ለማናገር እንደምንወጣም ከወዲሁ እንገልጻለን ፡፡

4 ገጽ እና ከ350 በላይ የሰዎች ስም ዝርዝር አባሪ አድርገን ከዚህ የአቤቱታ ማመልከቻ ጋር አያይዘን አቅርበናል፡፡፡

የቤተክርስቲያን አምላክ ቤተክርስቲያንን ይጠብቅ!!!

ግልባጭ

 • ለቅዱስ ፓትሪያርኩ ልዩ ጽ/ቤት
 • ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
 • ለጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ
 • ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ህብረት
 • ለማህበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት
 • ለኢህአዴግ ጽ/ቤት
 • ለጠቅላይ ሚኒስቴር
 • በፍትህ ቢሮ የፀጥታዎች ጉዳይ ጽ/ቤት
 • ለፖሊስ ኮሚሽን ጽ/ቤት
 • ለፌዴራል የሃይማኖቶች ጉዳይ ጽ/ቤት

 • ሄኖክ ብርሃኑ
  ሄኖክ ብርሃኑ Ethiopia, Addis Ababa
  Oct 26, 2017
  Oct 26, 2017
  አንድ ነን
 • Tezera
  Tezera Germany, N
  Oct 25, 2017
  Oct 25, 2017
  የተዘረዘሩትን መንፈሳዊ ጥያቄዎች የኔም ጥያቄዎች ናቸው ሙሉ ድጋፌን ሰጥቻለሁ
 • Simon ketema
  Simon ketema United Kingdom, London
  Oct 21, 2017
  Oct 21, 2017
  Singture
 • ዋለልኝ ተፈራ
  ዋለልኝ ተፈራ Ethiopia, Addis Ababa
  Oct 20, 2017
  Oct 20, 2017
  የተጠየቀው ጥያቄ አሳሳቢና መሰረታዊ በመሆኑ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲጥ እንጠይቃለን።
See More
1255

Signatures

 • 5 months ago
  samuel Ethiopia
  5 months ago
 • 5 months ago
  ሄኖክ ብርሃኑ Ethiopia
  5 months ago
 • 5 months ago
  Tezera Germany
  5 months ago
 • 5 months ago
  Yehualashet bekele Ethiopia
  5 months ago
 • 5 months ago
  Eshetu Mesfin United States
  5 months ago
 • 5 months ago
  Eyob Ethiopia
  5 months ago
 • 5 months ago
  Simon ketema United Kingdom
  5 months ago
 • 5 months ago
  ዋለልኝ ተፈራ Ethiopia
  5 months ago
 • 5 months ago
  natnael amare Singapore
  5 months ago
 • 5 months ago
  ተረፈ ገዛኽኝ Ethiopia
  5 months ago
 • 5 months ago
  Tedla Kinfe Ethiopia
  5 months ago
 • 5 months ago
  Eyasu Singapore
  5 months ago
 • 5 months ago
  Jhonmehari Switzerland
  5 months ago
 • 5 months ago
  Diyakon yohannes Singapore
  5 months ago
 • 5 months ago
  Hailemariam wondwossen Ethiopia
  5 months ago
See More