Mahlet Nigatu 0

ብ/አ/አብርሃም በዲሲ ሀ/ስብከት የጀመሩት መስመር እስኪይዝ ጊዜ እንዲሰጣቸው እንለምናለን

8 people have signed this petition. Add your name now!
Mahlet Nigatu 0 Comments
8 people have signed. Add your voice!
8%
Maxine K. signed just now
Adam B. signed just now

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የጸሎታችሁ በረከት ትድረሰን እኛ በዲሲና አካባቢው የምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፤ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮችና የምዕመናን ተወካዮች ረቡዕ ጥቅምት 16 ቀን ባደረግነው አስቸኩዋይ ስብሰባ ለብፁዓን አባቶቻችን የሚከተለውን ተማጽኖ ስናቀርብ በታላቅ ትህትና ነው፡፡ ባለፈው ዓርብ ጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም. የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን እያሳለፈ መሆኑን በአንክሮ እየተከታተለን ነው፡፡ ጥቅምት 16 ቀን በጳጳሳት ዝውውር እና ምደባ ላይ በቅዱስ ፓትርያርኩ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ አብርሃም መካተታቸውን በመረዳታችን ይህን የተማጽኖ ደብዳቤ ለብፁዓን አባቶቻችን ለማቅረብ ተገደናል፡፡ ብፁዕ አባታችን አቡነ አበርሃም የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሁነው ከተመደቡበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ሀገረ ስብከቱን ለማጠናከር ይህ ነው ተብሎ በቃላት ለመግለጽ የማይቻል መስዋዕትነትን ከፍለዋል አሁንም እየከፈሉ ነው፡፡ሀገረ ስብከቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከተቋቋመ ጥቂት ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም በሀገረ ስብከቱ ተመድበው ለሚመጡ ብፁዓን አበው ማረፊያ ቤት ማለትም መንበረ ጵጵስና ባለመኖሩ ሀገረ ስብከታቸው ከነበረው ከኒውዮርክ ድረስ በህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ እየተመላለሱ በዲሲና አካባቢው ያሉ ምእመናንን በማስተባበር የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት መነበረ ጵጵስና እንዲኖረው አድርገዋል፡፡ ወደ ዲሲና አካባቢው ከተዘዋወሩም በኋላ የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያንን በመትከል በደሲና አካባቢው ያሉ ምእመናንን ትክክለኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና በሚፈቅደው መልኩ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማድረጋቸው በተጨማሪ ለህዝበ ክርስቲያኑ ዘወትር እሁድ ትክክለኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያን እምነትና ሥርዓት ምን እንደሆነ እያስተማሩ ምእመኑ ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ሥርዓትና እምነት ግንዛቤ እንዲያገኝ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ቀድሞ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ግዜ እንዲሁም ወደ ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከተዘዋወሩ በኋላ ከሰሩዋቸው ዓበይት ተግባራት መካከል፤- • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዋቅር የታቀፉ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን ተክለዋል፡፡የቺካጎ ሚካኤል፤የኦሀዮ ገብርኤል፤ የሳውዝ ዳኮታ ኪዳነ ምሕረት፤ የአትላንታ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፤የኖርፎልክ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፤የቨርጂንያ ረጉኤል ፤የኖርዝ ካሎራይና በዓታ ለማርያም፤የኬንታኪ ገብርኤልናየመንፊስ ቅድስት ፣ማርያም ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ • እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ገለልተኛ የነበሩ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ምእመናንንና የቦርድ አስተዳደሮችን ባላቸው የማግባባት ተሰጥኦ ቀርበው እውነታውን ገልጠው በማስታወቅ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያናቸው እንዲገቡ አድርገዋል እያደረጉም ይገኛሉ ለምሳሌነት ኦክላሆማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ና የኖርዝ ካሮላይና እግዚአብሄር አብ ይጠቀሳሉ፡፡ • ፈርሶ ሊወድቅ ደርሶ የነበረውን የኒዎርክ ሀገረ ስብከት ሕንጻ ራሳቸው እንደ አንድ ሰራተኛ በመሆን ልዩ አድርገው በማሳደስ • በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት በካህናትና በምእመናን መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ፈጥኖ በቦታው በአካል ተግኝተው መፍትሄ በመስጠት • በሰንበት ት/ቤት አንድነት ጉባኤ በመገኘት ወጣቱ ለቤተክርስቲያን አንድነት እንዲቆሙ በማድረግ • በገለልተኝነት ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን በተለያያ ግዜ ለውይይት በመጋበዝ ወደ መስመሩ እንዲመጡ ጥሪ በማድረግ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያለችበት ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑ ከእናንተ አባቶቻችን የተሰወረ አይደለም ከዛሬ አራትና አምስት ዓመት በፊት ካለው አሁን ያለው ለውጥ ከፍተኛም ቢሆንም ለዚህ ለውጥ መምጣት ደግሞ ፋና ወጊ የሆኑት ብፁዕ አባታችን አቡነ አብርሃም መሆናቸውን ስንመሰክር በልበ ሙሉነት ነው፡፡ስራው ተጀመረ እንጂ አልተገባደደም ገና ብዙ መስዋዕትነትን ይጠይቃል በዲሲና አካባቢው ያለን ካህናትና ምዕመናን በብፁዕ አባታችን መሪነት ሀገረ ስብከቱን ለማደራጀት፤ የራሳችንን ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት እንዲሁም በአስተዳደር ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተለዩትን ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር የሚመጡበትን ሁኔታ በማጠናከር ላይ ሳለን ይህ አስደንጋጭና ተስፋ አስቆራጭ ዜና በመሰማቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች የሆነውን ሁሉ አሳዝኖናል፡፡ ስለዚህ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በአርቆ አሳቢነታችሁ ተረድታችሁ ብፁዕ አባታችን የጀመሩትን ሥራ ይፈጽሙ ዘንድ ባሉበት ሀገረ ስብከት እንዲቆዩ በትህትና እናመለክታለን፡፡ ቡራኪያችሁ አይለየን፡፡

Links

http://eotcdc.org
Share for Success

Comment

8

Signatures