Kale Heywet Renaissance 0

ተሓድሶ ይፋጠን፤ የቃለ ሕይወት ህልውናና ክብር ይጠበቅ!

23 people have signed this petition. Add your name now!
Kale Heywet Renaissance 0 Comments
23 people have signed. Add your voice!
3%
Maxine K. signed just now
Adam B. signed just now

አቤቱታ ለኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን መሪዎችና ሽማግሌዎች

ተሓድሶ ይፋጠን፤ የቃለ ሕይወት ህልውናና ክብር ይጠበቅ!

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን መሪዎችና ሽማግሌዎች

ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉዋትና ከአንጋፋ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አንዱዋ የሆነችው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የምትታወቀው በተጠያቂነት ባህሏ ነው፡፡ ኃላፊነትና ተጠያቂነትም ከእሴቶችዋ አንዱ ነው፡፡ ዳሩ ግን ይህ ባሕልና እሴት ከተወሰኑ አመታት ወዲህ እየተዳከመ በመምጣቱ ለዚህ ዓለም ብርሃንና ጨው እንድትሆን የተጠራችው ቃለ ሕይወት ጨውነትዋንና ብርሃንነትዋን እንድታጣና የክርስቶስ እውነተኛ ምስክር እንዳትሆን የሚያደርጉ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ነገሮች በውስጥዋ እየተስተዋሉ ይገኛል። ከዚህም የተነሳ የቤተ ክርስቲያናችን ስዕል ከጊዜ ወደ ጊዜ በመንግሥት፣ በረጅዎቻችንና በሌሎችም አብያተክርስቲያናት ዘንድ እየቆሸሸና ተአማኒነቱዋንና ተጽእኖዋን እያሳጣት መምጣቱ እጅግ አስግቶናል። ይህ እንዲሆን ዋናው ምክንያት በልማት ኮሚሽኑና በጽሕፈት ቤቱ ውስጥ የአሰራርና የስነምግባር ብልሹነት ሥር መስደዱ እንደሆነ ስለተረዳን እንደ ቃለ ሕይወት አባላት ያን ተረድተን ዝም ማለት ትክክል እንደሆነ ስለማናምን ይህንን አቤቱታ ለመላክ ተገደናል፡፡ ጥያቄዎቻችንን እንደሚከተለው አቅርበናል።

  • የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ለድሃ ኢትዮጵያዊያን እርዳታ በመለገስና የልማት ስራዎችን በመስራት የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሌሎች ለማካፈልና የሀገራችንንም ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ በዓለም ዙሪያ ካሉት ከተለያዩ ረጅዎች ለምና የምታመጣው ገንዘብና ንብረት ለታለመላቸው ሰዎች በአግባቡ አለመድረሱና ያ ገንዘብና ንብረት ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችንን የሙስናና የምዝበራ ዋሻ እንድትሆን ሲያደርግ አይቶ ዝም ማለት ክርስቲያናዊና የዜግነትን ኃላፊነት በአግባቡ አለመወጣት ብቻ ሳይሆን በክርስቲያንና ክርስቲያን ባልሆነውም ዓለም ተቀባይነት ካለው የሥነ ምግባር ሕግ ጋር የሚቃረን ስለሆነ አስቸኳይ እርምት እንዲደረግ እንጠይቃለን፤
  • ከዚህም ጋር በተያያዘ አጋር ድርጅቶች ድጋፍ በማቆማቸው በጽህፈት ቤታችንና በተለያዩ ፕሮጄክቶች ያሉ ብዙ ሰራተኞች ስራና ደመወዝ ቆሞባቸው እየተንገላቱ ስለሆነና ብዙዎችም ድሆች እየተጎዱ ስለሆነ ረጂዎች ድጋፍ እንዲለቁና የቆሙት የልማት ስራዎችም እንዲቀጥሉ ተገቢ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን።
  • በዋናው ጽሕፈት ቤታችን የተወሰኑ ግለሰቦች ለድሃ ድሃ የመጣውን እርዳታና የቃለ ሕይወትን ሀብት በመጠቀም በቀጠናዎቻችንና በተለያዩ ቦታዎች በጎ ያልሆነ የተጽዕኖ መረብ እንዲዘረጉና ደጋፊዎችን በማደራጀትና በዓለም ዙርያ ካሉ ረጅዎች የሚላከውን ገንዘብና ንብረት ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች ምርጫ ቅስቀሳ በመጠቀም የራሳቸውን መንግሥት እንዲገነቡ ዝም መባሉ ቃለ ሕይወትን በእጅጉ እየጎዳት ስለሆነ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን፤
  • በቃለ ሕይወት ጽሕፈት ቤት ጥቂት ግለሰቦች አማኞችን አፍራሽ በሆነ መንገድ በዘርና በክልል በመለያየትና በመከፋፈል ፤ በፍቅርና በመንፈስ አንድነት እንዳንተሳሰር አንዳችንን ከሌላችን ጋር እያጋጩንና አንዳችን ሌላችንን እንደ እህትና ወንድም ሳይሆን እንደጠላት እንድናይ እያደረጉን በውሸት ወሬና እጅግ በረቀቁ ስልታዊ ዘዴዎች ቃለ ሕይወትን ወደ ውድቀት እየወሰዱአት ስለሆነ የዚህ ዓይነት ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን፤
  • ቤተ ክርስቲያናችን የወንጌል ሥራ ቁንጮ አገልግሎትዋ የሆነ፤ ለቅድስናና ለሕይወት ጥራትና ዕድገት ማዕከላዊ ቦታ የምትሰጥ ሆና መቀጠል ሲኖርባት በጽህፈት ቤታችን ሞራላዊ ዝቅጠት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥር እየሰደደ ስለሄደ ይህን የማስቆምና ጽህፈት ቤታችንን የማጽዳት እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን፤

ውድ የተከበራችሁ የቤተ ክርስቲያናችን መሪዎችና ሽማግሌዎች፤

ቃለ ሕይወት ከአሰራርና ከስነ ምግባር ብልሹነት የጸዳች ፤ቅድስትና ንጽህት የክርስቶስ ሙሽሪት፥ ብሎም በሀገራችንና በዓለም ሁሉ የእግዚአብሔር መንግስት ነፀብራቅና የሞራል ልዕልና ፈጣሪ እንድትሆን ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች ምክንያት በሆኑት በጽህፈት ቤታችንና በልማት ኮሚሽኑ አመራር ላይ በአፋጣኝ ተገቢ እርምጃ ተወስዶ ቤተክርስቲያኒቱን በአደራ የሚመራ ገለልተኛ አካል ተሰይሞ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች ሁሉ በአስቸኳይ እንዲስተካከሉና ተአማኝነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድ እኛ የቤተክርስቲያኒቱ አበላት በስማችንና በፊርማችን እንጠይቃለን።

‘የቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ማንኛውም አባል የቤተክርስቲያንን ሕልውና የሚነካ ጉዳይ ተከስቶ በሚያይበት ጊዜ ጉዳዩ እርምት እንዲያገኝ በየእርከኑ ላሉ የስራ አስፈፀሚ በማስረጃ አስዳግፎ ማቅረብ ይችላል፡፡’ (የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን 2006 የተሻሸለው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ አንድ መቶ ስድስት፤ የአባላት ልዩ ተሳትፎ)

እግዚአብሔር ቃለ ሕይወትን ይባርክ!

ጥር 2011 ዓ.ም

አቤቱታ ለኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን መሪዎችና ሽማግሌዎች (2006 በተሻሸለው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 106 መሰረት)

Share for Success

Comment

23

Signatures