Tewodros Birhanu 0

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

554 people have signed this petition. Add your name now!
Tewodros Birhanu 0 Comments
554 people have signed. Add your voice!
56%
Maxine K. signed just now
Adam B. signed just nowየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት

ቀን 14/01/2008

ቁጥር 00/68/ማ/ህ/2008

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- በተሀድሶ መናፍቃን ላይ የወጣ የተቃውሞ የአቋም መግለጫ፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብዙ የመከራ ዘመናትን አሳልፋለች ቀጥሎም ብዙ ዘመናትን ተሻግራ ይኽኛውን ትውልድ ታስተምራለች ምክንያቱም ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት ስለሆነች ነው፡፡

ንጽህት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት መሆኑ በመጽሐፍ ቅድስ ተጽፏል፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከጠላት ውጊያ ተለይታ የኖረችበት ዘመን የለም ወደፊትም አትኖርም መሰረቷ አይናወጥምና፡፡ እነዚህን የመከራ ዘመናትን ባለጊዜው ትውልድ ለችግሮቹ መፍትሔ እያበጀ መስዋእትነትን እየከፈለ እዚህ ዘመን ላይ እንዲደርስ የግዴታውን ተወጥቷል፡፡

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀደምት አበው ግዴታቸውን ተወጥተው ማለፋቸውን ከእናንተ ተምረናል፡፡

በዚህ ዘመን ያላችሁ አባቶቻችን ቤተክርስቲያን የማስተዳደር ግዴታው ኃላፊነቱ በእናንተ ላየ እንደተጣለ ስለምናምን ነው፡፡ ነገር ግን በምዕመናን መካከል ከዶግማ ጀምሮ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ እየተፋለሰ በመሆኑ የሰልስቱ ምዕት ትምህርት ቀርቶ የሉተር አስተምህሮ በሰፊው እየታየ ነው፡፡

ስለዚህ የቀደሙት አባቶቻችን ልጆች እንደመሆናችሁ እኛ ደግሞ የእናንተ ልጆች እንደመሆናችን ከጥቅምት 12 ቀን የሚጀመረው መንፈስ ቅዱስ ለሚመራው ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እግዚአበሔር መርጦ የሾማችሁ ባለአደራ አባቶቻችን ከእኛ ከልጆቻችሁ ከምዕመን የሚቀርበውን ኃይማኖታዊ ጥያቄ ተመልክታችሁ ውሰኔ እንድትሰጡን ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም በትህትና እንጠይቃለን፡፡

ጥያቄ

  • ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ በፊት ውግዘት ያስተላለፈባቸውን ግለሰቦች ሆኑ ማህበራት ለምዕመን በግልጽ በሚዲያ እንዲተላለፍ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
  • ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምሮ ውጭ የምንፍቅና ትምህርት የሚያስተላልፉትን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊት የሚያፋልሱትን በተሳሳተ መንገድ እያስተማሩ ያሉ ሰዎች እንዲወገዙልን፡፡
  • የቤተክርስቲያኒቷ ሦስቱን መንፈሳዊ ኮሌጅ መናፍቃን ባልታወቀ መንገድ ሰርገው ስለገቡ እነዚህን መርምራችሁ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ የሚያስተምሩ መምህራኖችን እንዲሁም የኦርቶዶክስ ልጆች የሆኑ ተማሪዎች ብቻ እንዲማሩ እንዲደረግልን፡፡
  • የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሚለው ስያሜ በቤተክርስቲያኒቱ ሥርዓት ከቅዱስ ሲኖዶስ ፍቃድ ያላገኙ ከኢትዮጵያ ውጭ በአውሮፓ፣ በአፍሪካ በአረብ ኤምሬት የእምነት ተቋም ነን የሚሉ እንዲዘጉልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን፡፡
  • የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮ የሚያፋልስ የህትመት ውጤቶች ሲዲ፣ መጽሐፍ፣ መጽሔት እንዲወገዙ በትህትና እንጠይቃለን ወደፊትም ማንኛውም የህትመት ውጤት ያለቤተክርስቲያን ፈቃድ እንዳይታተሙ እንድታደርጉ እንጠይቃለን፡፡
  • ኢ.ቢ.ኤስ የሚዲያ ጣብያ የሚተላለፍ ታኦሎጎስና ቃለ አዋዲ የተሰኙ የቴሌቪዥን መርሃ-ግብሮች በቤተክርስቲያኒቱ ስም ምንፍቅናን እየዘሩና የቤተክርስቲያኒቷን ክብር እየነኩ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ይኽን ተመልከቶ ስርጭታቸው እንዲያሳግድልን እንጠይቃለን፡፡

በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኒቷ ከላይ የገለጽናቸውን ችግሮች ሲኖዶሱ በትኩረት ተመልክቶ ውሳኔ እንዲሰጥልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን፡፡

‹‹የቀረውን ነገር ሳልቆጥር እለት እለት የሚከብደኝ የአብያተክርስቲያናት ሁሉ ሀሳብ ነው፡፡››

2ኛ ቆሮ. ፲፩፡፳፰

ብሯኪያችሁ ይደርብን፡፡

እግዚአብሔር ሀገራችንን እና ቅድስት

ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- +251 911355038/+251911860603

Share for Success

Comment

554

Signatures