stop Aba Gerima from bexoming bishop

156 people have signed. Add your voice!
16%
Maxine K. signed just now
Adam B. signed just now

የአባ ገሪማን እጩ ጵጵስና በማስቆም ቤተ ክርስትያንን ከከፋ አደጋ እንታደግ !

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ፤ አሜን፡፡

አባ ገሪማን አንዳንድ አካላት ለጵጵስና ማጨታቸውን ስለተረዳን በእርሳቸው ምክንያት ወደፊት ሊፈጠር የሚችለውን የከፋ አደጋ ለመከላከል ሁሉም የሚመለከተው አካል ግንዛቤ እንዲወስድ በእንግሊዝኛ ከተጻፈው ኣቤቱታ ከተዘረዘሩት ነጥቦች በተጨማሪ የተዘጋጀ ሐተታ ነው፡፡


አሁን በምዕራብ አውስትራሊያ ፐርዝ ከተማ በደብረ መድሐኒት መድሀኒያለም ቤተክርስትያን አገልጋይ የሆኑት አባ ገሪማ አንለይ ተስፋየ ለአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ጳጳስ ኢንዲሆኑ ለማድረግ አንዳንድ አካላት በዕጩነት ጠቁመዋቸው ቅስቀሳ እያደረጉ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ እነዚህ አካላት ወደፊት ለሚፈጠረው ችግር ግድ ሳይላቸው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በሩቅ የሚያውቋቸውና የእሳቸውን ክፉ ስራና አኩይ አላማ ሳይረዱ በቅንነት ተነሳስተው መለኩሴ ነኝ ስላሉ ብቻ ጳጳስ እንዲሆኑ የሚፈልጉ ናቸው፡፡ የጨበጡት መስቀልና ልብሰ ተክህኖኣቸው ይከበራልና፡፡


ለመሆኑ ኣባ ገሪማ ማን ናቸው?

አባ ገሪማ ወደ ምንኩስና አለም ከመምጣታቸው በፊት የነበሩበትን ታሪክ ወደፊት በመረጃ ተደግፎ ይቀርባል። ከራሳቸው ኣንደበትና በሚያውቋቸው ኣባቶች እንደሚባለው የኣባ ጳውሎስ የቅርብ ወዳጅ እንደነበሩ ግልፅ ነው።

ለአቡነ ጳውሎስ ታማኝ ካድሬ ሁነው የፈጸሙትን ብዙ ግፍ እውነቱን ማወቅና ማጣራት ለሚፈልግ አዲስ አበባ በአስተዳዳሪነት ወዳገለገሉባቸው ኣብያተ ክርስትያናት ስልክ ቢደውል ሁሉንም መረጃ በቀላሉ ማግኘት ይችላል፡፡ አባ ገሪማ ቤተ ክርስትያንን መከፋፈል የጀመሩት ገና በአዲስ አበባ የካራ አሎ መድሃኔ አለምና ስላሴ ቤተ ክርስትያን አስተዳዳሪ ሁነው እንደተሾሙ ነው፡፡ ቤተ ክርስትያኑን ለሁለት በመክፈል መድሃኔ አለምን ቤተ ክርስትያ የአቡነ ጳውሎስ ገዳም ስለሆነ መለኩሴ ብቻ እንጅ ካህናት አይቀድሱበትም በሚል ካህናትን አግልለው በሰላም ይኖር የነበረውን የቤተክርስትኗን ማህበረሰብና ካህናትን ለሁለት በመክፈል እርስ በእርስ በማጋጨት አዳክመውና ከፋፍለው በመግዛት የወያኔንና የአቡነ ጳውሎስን የአስተዳደር ዘይቤ ስራ ላይ በማዋል በብዙ ካህናት ላይ ብዙ ግፍ ፈጽመዋል፡፡

በ1997 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በተደረገው ታሪካዊ ምርጫ ከቤተ ክህነት በታዛቢነት የአቡነ ጳውሎስ ወኪል ሁነው ልደታ አካባቢ ተመድበው ባቀረቡት ሪፖርት ምርጫውና አፈጻጸሙ ፍጹም እንከን አልባና በዲሞክራሲያዊነቱና ፍትሀዊነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ነው በማለት ሪፖርት ካቀረቡ ካድሬ መነኮሳት አንዱና ዋናው ናቸው፡፡ ይህንንም ዛሬ ድረስ ሳያፍሩ በኩራት የሚያወሩት ነው፡፡ በዚህ ምርጫ ምክንያት በብዙ መቶዎች ሲገደሉና በብዙ ሽዎች ሲታሰሩ እሳቸው ለአቡነ ጳውሎስና በቤተ ክህነት ዙሪያ ለመሸጉት የወያኔ ካድሬዎች ለዋሉት ውለታ በሹመት ወደ ጀርመን ተላኩ፡፡

ጀርመን አገር ከምእመኑ ጋር በገቡት ግጭትና ሰበካ ጉባኤውን እና ምእመኑን በመከፋፈል የቤተ ክርስትያኑን ሰላም ነስተው የጥላቻ ማዕከል በማድረጋቸው ከምዕመናን ክስ ሲቀርብባቸው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው እንዳይጠሩ በመስጋት ወዲያውኑ አማራጭ ሲፈልጉ አጋጣሚው ፐርዝ ደብረ መድሃኒት መድሃኔ አለም ቤተ ክርስቲያን ካህን የሚፈለግበት ጊዜ ስለነበረ የካህን እጥረቱን ለመቅረፍ ሲባል ብቻ በችኮላ አጠቋቆማቸው እንኳ እስካሁን ድረስ ግራ አጋቢ በሆነ ሁኔታና ማንነታቸው በአግባቡ ሳይጣራ ተቀጥረው ወደ አውስትራሊያ ፐርዝ ከተማ መጡ፡፡

እሳቸው ፐርዝ ከመጡ ጀምሮ በርካታ ምእመናንና አገልጋይ ዲያቆናት በእሳቸው የተንኮል ስራ እየተማረሩ ከቤተክርስትያን ለቀዋል፡፡ ከእሳቸው ጋር በተፈጠረ ጠብም ምክንያት የመድሃኔ ዓለም ቤተክርስትያን ለሁለት ተከፈለ፡፡ ምእመናንም ለሁለት ተከፍለው በአለማዊ ፍርድ ቤት ተካሰው በመቶ ሽዎች የሚቆጠር የቤተክርስትያን ገንዘብ ለፈረንጅ ጠበቃና ለፍርድ ቤት ክፍያ ተከፍሎ ባክኗል፡፡ የአንድ አገር ልጆች ሌላ የሚለያየን ምክንያት ሳይኖር፣ ሁላችንም ስደተኛው ሲኖደስ ህጋዊ ነው ብለን የምናምንና በፖለቲካ አቋማችንም አሁን በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ተወግዶ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት አለበት ብለን የምናምን ሁነን ሳለ በእሳቸው ምክንያት ለሁለት ተከፍለን በጠላትነት እንድንተያይ አድርገውናል፡፡

እንግዲህ እንዲህ አይነት ሰው ነው በስመ መነኩሴ ለጵጵስና ታጩ የተባለው፡፡ መቸም ቅዱስ ሲኖዶስ ጳጳስ ሲሾም በምን መስፈርት እንደሚመርጥ ከእኛ ከምእመናን ወደላይ ወደ ቅዱስ ሲኖዶሱ ምክርና ሀሳብ መስጠት ለቀባሪው አረዱት ስለሚሆንብንና ድፍረትም ስለሚሆንብን ይህንን አናደርገውም፡፡ ነገር ግን በቡድንና በቲፎዞ እየተደረገ ያለው ሩጫ ተጽዕኖ ፈጥሮበት ተገቢውን ማጣራት ሳያደርግ እንዲሁ በይሁን ይሁን በመጓዝ ወደፊት የሚያስጸጽተው ከባድ ስህተት ውስጥ እንዳይወድቅ እኛ ከመለኩሴው ጋር እየኖርን ያለን ምእመናን የምናውቀውንና እየደረሰብን ያለውን እውነታ ጥቂቱን ብቻ አሳጥረን ከዚህ በታች አቅርበናል፡፡

የሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆናችሁ ብጹዓን ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣ መነኮሳትና ካህናት፤ እንዲሁም የተከበራችሁ የእጩ ጳጳሳት አቅራቢ ኮሚቴ አባላት፣ እና በአውስትራሊያ በተለያዩ ከተሞች በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር ባሉ ቤተክርስትያናት የምታገለገሉ ካህናትና ምዕመናን የሚከተሉትን ሶስት ነጥቦች ስለ እውነት ስትሉ በቅንነትና በትኩረት እንድትመለከቱልን በመድሐኒያለም ስም እንለምናለን፡፡

  1. አባ ገሪማ ለህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ታማኝ አይደሉም፤ በህጋዊነቱም አያምኑም፡፡ ስደተኛውንና ህጋዊውን ፓትርያርክን እና ቅዱስ ሲኖዶሱን በተደጋጋሚ ያጥላላሉ፡፡ እንዲሁም አዲስ አበባ ለመሸገው ሕገ ወጡ የወያኔ-ኢህዓዴግ ሲኖዶስና ለሟቹ አጭበርባሪ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አድናቆታቸውንና ቅዱስነታቸውን በአደባባይ በመግለጽ ያወድሳሉ፡፡ በዚህ ነጥብ ስር እሳቸው ያደረጓቸውንና በሰው መሀል ከተናገሯቸው ውስጥ ነገር ላለማብዛት አራት ነጥቦችን ብቻ አሳጥረን እንደሚከተለው አቅርበናቸዋል፡፡

1.1 አቡነ ጳውሎስ በሞቱ ሳምንት ቅዳሜ ምሽት በመድሐኒያለም ቤተ ክርስትያን በር ላይ ምእመናን ሰብሰብ ብለው ስለ አቡነ ጳውሎስ ሞትና ስለ እግዚአብሄር ስራ ሲወያዩ እሳቸው ጣልቃ ገብተው "የኢትዮጵያ ሕዝብ እኮ ደንቆሮ ነው፤ አቡነ ጳውሎስን የመሰለ አባት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ታሪክ አልተፈጠረም፣ ወደፊትም አይመጣም፡፡ "ይህ ደንቆሮ ሕዝብ እኒህን የመሰሉ የተማሩና አርቆ አሳቢ ቅዱስ አባት ሳይጠቀምባቸው አለፉ" ብለው ተናግረዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ይኸን ንግግራቸውን ተቃውመው መልስ ለሰጧቸው ግለሰቦች እናንተ ይኸን የሚወራውን ፖለቲካ ይዛችሁ ነው፣ እኔ አባቴ ስለሆኑ ውስጡን አውቃለሁ" ብለው መልሰዋል፡፡

1.2 ለአገልግሎት ወደ ሲድኒ ማርያም ተጋብዘው ሲድኒ ከተማ በሄዱ ጊዜ አንድ ምዕመን ቤት ማታ በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ስለ ቅዱስ ሲኖዶሱ ውይይት ተነስቶ ሀሳቦች በሚንጸባረቁበት ጊዜ "ፓትሪያሪኩ (ስደተኛውን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማለታቸው ነው) ከሞቱ በቦታቸው ሌላ ፓትርያርክ ሊሾም አይገባም፡፡ ቤተክርስትያን ለሁለት የተከፈለችው በእሳቸው መሰደድ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ እሳቸው ሲሞቱ አሁን በስደት ያሉት ጳጳሳት ወደ አዲስ አበባው ሲኖድስ ተጠቃለው መግባት ነው ያለባቸው፡፡' በማለት የህጋዊውን ሲኖዶስ ህጋዊነትና ቀጣይነት ምእመኑ እንዲጠራጠር ለማድረግ ቀስቅሰዋል፡፡

1.3 በተለያየ ጊዜ ፐርዝ መድሐኒያለም ቤተ ክርስትያን ሲያስተምሩ "ስደተኛ ሲኖዶስ ተብየው ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው፤ ሲኖዶስ የሚያሰኘው ምንም አይነት የቤተ ክርስትያን መዋቅር የለውም፡፡ ምኑም አይረባም፤ ሲኖዶስ ማለት አገር ቤት ያለው ነው፡፡ የቤተ ክርስትያን መዋቅር ያለውና ቤተ ክርስትያንን የሚቆጣጠር አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ ነው' በማለት በተለያየ ጊዜ እየደጋገሙ ይናገራሉ፡፡ ይህንን የመድሐኒያለም ቤተ ክርስትያን ምዕመናንም ሆኑ በእሳቸው ምክንያት ከዚያ ወጥተው የቅዱስ ገብርዔል ቤተ ክርስትያንን ያቋቋሙ ምእመናን የሚያውቁት ሀቅ ነው፡፡

1.4. የፐርዝ መድሀኒያለም ቤተ ክርስትያን ከገለልተኛነት ወደ ህጋዊው ሲኖዶስ መዋቅር ተጠቃሎ ሲገባ ውሳኔ በሚወሰንበት ጊዜ እሳቸው በወቅቱ ሌላ ቦታ ስለነበሩ በሚመለሱበት ጊዜ ውሳኔው ሲነገራቸው ተናደው እኔ በስብሰባው ብኖር ኑሮ ይህን ውሳኔ አላስወስናችሁም ነበር፤ በማለት ለህጋዊው ሲኖዶስ ያላቸውን አቋም በአውደ ምህረት ላይ ቁመው ገልጸዋል፡፡

2. ለማስተዳደር የሚከተሉት ስልት የአቡነ ጳውሎስ ካድሬ በነበሩበት ጊዜ በካድሬነት የሰለጠኑበትን የከፋፍለህና አዳክመህ ግዛ የአመራር ዘይቤ ነው፡፡ አባ ገሪማ በሚያገለግሉበት ቤተ ክርስትያን ምእመኑን እርስ በርስ በመከፋፈልና በማጣላት ቤተ ክርስትያንን በመከፋፈል አንድነታችንንና ህብረታችንን እያዳከሙ ነው ያሉት፡፡

አባ ገሪማ የተካኑትን የወያኔንና የአቡነ ጳውሎስን የብሄር ፖለቲካ በስራ ላይ በማዋል በመድረክ ላይ ሲያስተምሩም ሆነ በማህበራዊ ጉዳዮች ከተለያዩ ምዕመናን ጋር ሲገኛኙ የብሄር ጉዳይ እያነሱ በቀድሞ ጊዜ እከሌ ብሄር ለምስክርነት እንኳ አይጠራም፡፡ የእከሌ ብሄርን ጉራና ትምክህት ነው መስማት ያስጠላኝ፡፡ የእከሌ ብሄር ተወላጆች ለፍታችሁ የመሰረታችሁትን ቤተ ክርስትያን ሊቆጣጠሩና እናንተን እንዲህ ሊያደርጓችሁ ነው፡፡ የእከሌ ብሄር ተወላጆች እናንተን ይንቋችኋል፣ ወዘተ እያሉ እየቀሰቀሱ ምእመኑ እርስ በእርስ እንዳይግባባና በጥላቻ እንዲተያይ በማድረግ ተከፋፍሎ የእሳቸው ብልሹ አስተዳደር እስረኛ እንዲሆንና በቤተ ክርስትያኑ ጉዳይ ላይ ተወያቶ አንድ ወጥ አቋም እንዳይኖረው በማድረግ ምእመኑን የእሳቸው መጫወቻ አድርገውታል፡፡

ከላይ በመግቢያው እንደጠቀስነው የአንድ ቤተ ክርስትያን ምእመናን ለሁለት ተከፍለን በአለማዊ ፍርድ ቤት ተካሰን በመቶ ሽዎች የሚቆጠር የቤተክርስትያን ገንዘብ ለፈረንጅ ጠበቃና ለፍርድ ቤት ክፍያ ተከፍሎ ባክኗል፡፡ እኛ የአንድ አገር ልጆች የሆንን የአንድ ቤተ ክርስትያን ምእመናን ሌላ የሚለያየን ምክንያት ሳይኖር፣ ሁላችንም ስደተኛው ሲኖደስ ህጋዊ ነው ብለን የምናምንና በፖለቲካ አቋማችንም አሁን በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ተወግዶ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት አለበት ብለን የምናምን ሁነን ሳለ በእሳቸው ምክንያት ብቻ ለሁለት ተከፍለን በጠላትነት እንድንተያይ አድርገውናል፡፡ የፐርዝ ደብረ መድሐኒት መድሐኒያለም ቤተ ክርስትያን ምእመናን በመካከላችን የሚያጣላን አንዳችም ምክንያት ሳይኖር እሳቸው ቡድን ፈጥረው በሚያደርጉት የዘር ቅስቅሳ የተነሳ ቤተ ክርስትያኑ ለሁለት ተከፍሎ ሌላ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ተፈጥሯል፡፡ አሁንም እሳቸው ይዘውት የቀሩት የመድሐኒያለም ቤተ ክርስትያን ምዕመን በእሳቸው ምክንያት በሁለት አቋም ተከፍሎ ለመከፋፈል ቋፍ ላይ ከመድረሱም በላይ አሁን በቅርብ ጊዜ ቤተ ክርስትያኑ ውስጥ ድብድብ ተፈጥሯል፡፡

እኒህ መነኩሴ ሌላው ቀርቶ በንስሀ አባትነት የተነገራቸውን የቤተሰብ ሚስጥር ሳይቀር ወደ አደባባይ እያወጡ እከሌ በእከሌ ላይ እንዲህ አድርጓል እያሉ እያወሩ ምእመኑን እርስ በእርሱ ያጣላሉ፡፡ ባልና ሚስትን ያፋታሉ፡፡ ባል ወይም ሚስት ተበደልሁ ምከሩልኝ ብሎ በአባትነት ሲጠይቃቸው መክረውና ገስጸው ከማስታረቅ ይልቅ ለምን አትፈችውም፣ ወይም ለምን አትፈታትም እያሉ ያፋታሉ፡፡ ባለትዳሮችን ከአንዱ ነጥቀው ለሌላ ያጋባሉ፡፡ እሱ ወይም እሷ እኮ እንዲህ ያደርጋል ወይም ታደርጋለች በማለት እጮኛሞች ጋብቻቸውን እንዲሰርዙ ያደርጋሉ፡፡

3. እግዚአብሄር ለቤተ ክርስትያናችን ተጨማሪ አገልጋይ ሲያመጣ እንደ ተቀናቃኝ በመቁጠር ወደ ቤተክርስትያን እንዳይገባ ቲፎዞዎቻቸውን አደራጅተው ሆን ብለው የሀሰት ወሬ እየፈጠሩ በማሰራጨት ቤተ ክርስትናችንን እያመሱና ተጨማሪ አገልጋይ እንዳያገኝ እያደረጉ ነው፡፡ አሁን በቅርቡ እንኳ መምህርና ካህን የሆነ አገልጋይ በጋብቻ ምክንያት ወደ አውስትራሊያ ወደ ፐርዝ ደብረ መድሐኒት መድሐኒያለም ቤተ ክርስትያን ሲመጣ ገብቶ ከቀደሰና ካስተማረ በእኔ ህልውና ላይ አደጋ ይሆናል ብለው በመፍራት ብቻ ጥቂት ቲፎዞዎቻቸውን ይዘው ያለ ስሙ ስም በመስጠትና የሀሰት ወሬ ፈጥረው በማስወራት አዲሱ መምህርና ካሕን ተማረው ከቤተ ክርስትያን እንዲርቁ በማድረግ ቤተ ክርስትያናችን በእኒህ መነኩሴ ምክንያት አገልጋይ እንዲያጣ ተደርጓል፡

የተከበራችሁ ብጹዓን ጳጳሳት፣ አባቶች መነኮሳትና ካህናት፣ እንዲሁም በተለያዩ የአውስትራሊያ ግዛቶች የምትገኙ ምዕመናን በቸልተኝነት ልታልፉት የማይገባ አንድ ነጥብ አለ፡፡ እሱም ከዚህ ቀደም አውስትራሊያን ደርበው በጵጵስና ሲያገለግሉትና ሲመሩት የነበሩት ጳጳስ የማስተዳደር ድክመት ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ በእሳቸው የአስተዳደር ዘመን ተከስተዋል ለሚባሉ የአመራር ድክመቶች የሚሰጠው መፍትሄ ግን ከድጡ ወደማጡ መሆን የለበትም፡፡ እሳቸውን አንስቶ ልቡ በአቡነ ጳውሎስ ፍቅር ያበደና ሀሳቡ ሁሉ አዲስ አበባ ወያኔ ሰራሹ ሲኖዶስ ጋ የሆነ፣ የሚያስተዳድረውን ቤተክርስትያን ምዕመን እየከፋፈለና እርስ በእርስ ዕያጣላ አንድ ቤተ ክርስትያንን ለሁለትና ሶስት የሚከፍልና ቤተክስትያናትንና ህጋዊውን ሲኖዶስ የሚያዳክም ሰው በስመ መነኩሴ ጳጳስ አድርጎ መሾም እብደት ነው፡፡

እኛ በአውስትራሊያ ፐርዝ ከተማ የምንገኝ ምእመናን በጵጵስና ሊሾምልን የሚገባው አባት ፈሪሀ እግዚአብሄር ያለውና ለተሾመበት አላማ ታማኝ የሆነ፤ እንዲሁም ምእመኑን ሳይከፋፍል ሁሉንም እኩል በአባትነት ይዞ እያነጸና እያስተማረ ቤተ ቤተክርስትያናትን የሚያሳድግ እውነተኛ አባት መሆን አለበት ብለን እናምናለን፡፡

ይህ ሳይሆን ቢቀርና እኒህ አስመሳይና ተንኮለኛ መነኩሴ ጳጳስ ሁነው ቢሾሙ መዘዙ የከፋ ከመሆኑም ላይ በራሱ በቅዱስ ሲኖዶስ ላይም ብዙ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡ እንደማታደርጉት እናምናለን እንጅ ሹመቱ የቲፎዞ ስራና የቡድን መሰባሰቢያ ሁኖ አባ ገሪማን ጵጵስና እንዲቀቡ ብታደርጉ ጵጵስናቸውን መደራደሪያ አድርገው ሹመታቸውን አስጠብቀው ዘወትር ልባቸው ወደሚናፍቀው የወያኔ ስብስብ ሲኖዶስ ሲሸበለሉ ለማየት ሩቅ ጊዜ እንደማንጠብቅ እርግጠኞች ነን፡፡

ስለሆነም ፍርሀታችንን ተረድታችሁ እኒህን በእንከን የተሞሉ አስመሳይና ተንኮለኛ መለኩሴን ጉዳይ ሰከን ብላችሁ በድጋሚ እንድትመረምሩትና በቅዱስ ወንጌላችንና በፍትሀ ነገስቱ በተደነገገው መሰረት የተጣላውን የሚያስታርቅና የተከፋፈለውን ቤተ ክርስትያን መልሶ አንድ የሚያደርግ እውነተኛና ጥሩ አባት፣ እንድትሾሙልን በቸሩ መድሐኒያለም ስም ልመናችንን እናቀርባለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚበሔር!

In the Name of the Father, and of the Son and of the Holy Spirit, One God. Amen.

To the Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Church in Exile

Abune Mekarios - Arch Bishop of the Diocese of Australia

To the Bishophood Selection Panel

We the petitioners are members of the Ethiopian Orthodox Church within Australia and beyond and supporters of the Holy Synod in Exile through thick and thin. Our petition is against the selection of one, Komos Aba Gerima to the Bishophood of the Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Church in Exile.

Komos Aba Gerima, an Ethiopian Orthodox Monk with a dubious past, has been the administrator of Debre Medhanit Medhane Alem Church in Perth, Western Australia for the last seven years. This man is the epitomy of evil, an incarnate of the inverse of the teaching of our beloved Orthodox Tewahdo Faith, who by his documented acts and deeds, supported by witnesses and evidence has been wreaking havoc on the Ethiopian Orthodox Christian Community of Perth in Western Australia and through his disciples of evil has been planting seeds of division, disunity and racism throughout Australia and beyond.

As if the damage done by this man was not enough at the local level, and even before the gaping wounds that he inflicted on many innocent individuals heeled, we now sadly and with great disappointment learn that he has been chosen as one of the candidates to the bishophood of the Ethiopian Orthodox Church through the Legal Holy Synod in exile.

We simply request that the Holy Synod re-examine the documented written and video evidence that has been presented to it concerning the transgressions of this man. These evidences relate to his behaviour as the administrator of the Debre Medhanit Medhane Alem Church in Perth and as a member of the Arch Diocese of Australia.

The Legal Holy Synod in Exile have in your hand court documents of Komos Gerima applying for a court order to stop 14 members of the Debre Medhanit Medhane Alem Church from attending church services.

The Legal Holy Synod in Exile have a written evidence of how such an application that included 16 concocted and false charges against the members mentioned above was used to evict and cancel the membership of the founders of Debre Medhanit Medhane Alem Church who, later, by the Grace of God and with guidance and assistance from Arch Bishop Mekarios established the Debre Hayl Kidus Gabriel and Kidane Mhret Church.

The Legal Holy Synod in Exile have a video evidence of Komos Gerima rubbishing the Holy Synod in Exile and aggrandising the Patriarchate in Addis Abeba.

The Legal Holy Synod in Exile have a witness of his hate diatribe against Amhara people. For the sake of maintaining the honour and dignity of our church, we are limiting the disclosure of his many actions to the above four categories with the hope that the Holy Synod in Exile will find it suffice to cancel the appointment of Komos Gerima to become anointed as a Bishop of our Church and the Legal Holy Synod in exile.

It is common knowledge that the Legal Holy Synod in Exile has either organised or is party to six episodes of fact finding or reconciliation events relating to this controversial monk. Many fathers and elders of the our church including Arch Bishop Yosef, Aba G. Selassie, Aba Wolde Tinsay etc and other delegations have visited us and conducted several meetings at different times. All of these efforts to pacify, reconcile and reunite the followers of the Orthodox Tewahdo Faith (members of the Debre Medhanit Medhane Alem Church and the Debre Hayl Kidus Gabriel and Kidane Mhret Church) has been thwarted by Komos Gerima and his handful of followers. To this day, he continues to preach hatred, division, racism and his somewhat disguised but unwavering admiration (allegiance) to the Addis Abeba Patriarchate and illegal Synod.

We, the petitioners, followers of the Orthodox Tewado Faith, victims of Komos Gerima, or, in full direct or indirect knowledge of Komos Gerima's numerous transgressions, express our deep apprehension of Komos Gerima being selected for anointment as a Bishop. If this is to hold true, it would constitute the most unjust decision and an egregious abuse of the trust of the followers of the Ethiopian Orthodox Church in Perth, Western Australia and beyond.

We beg the Legal Holy Synod in Exile to re-examine the evidence presented to it and stop the selection and incumbent anointment of Komos Gerima as a Bishop of the Ethiopian Orthodox Church and the Legal Holy Synod in Exile. Komos Gerima's acts and deeds do not deserve the bestowing of such a holy and responsible position in our beloved Ethiopian Orthodox Church and the respected Holy Synod in Exile. Not unless you want us to be devided, disunited and lose trust in those who administer our faith.

Australia, 1st of January 2016

Share for Success

Comment

156

Signatures