A Call for Peace and Reconcilation in EOTC
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን
ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፮ ቀን ፪፻፻፬ ዓም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
“ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ ወኵሎ መራዕየ ዘሎቱ ሤመክሙ መንፈስ ቅዱስ ጳጳሳት ከመ ትርአዩ ቤተክርስቲያኑ ለክርስቶስ እንተ አጥረያ በደሙ”
“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለእራሳችሁ ተጠንቀቁ”
ግብረ ሐዋርያት ፳፥፳፷
በውጭ አገር የምንኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን ቤተክርስትያን ዛሬ ስላለችበት ሁኔታ ለመነጋገር ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲመለከታቸው የምንፈልጋቸውን ሃሳቦች ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን፦
በቅድሚያ በብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስትያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የዓለም የሰላም አምባሳደር ድንገተኛ ዕረፍት ምክንያት የተሰማንን ልባዊ ሃዘን እንገልጻለን። አምላካችን እግዚአብሔር የቅዱስነታቸውን ነፍስ በዐፀደ ሕይወት እንዲያሳርፍልን፣ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን እንዲቆጥርልን፤ መታሰቢያቸውንም ለበረከት እንዲያደርግልን የዘወትር ጸሎታችን ነው።
ብፁዓን አባቶቻችን፦ በእውነተኛ እይታ ቀርበን ቤተክርስትያናችን የተጓዘችበትን ያለፉትን ፳ ዓመታት ስንመለከት በእርግጥም እረኛዎችዋ የተከፋፈሉበት፣ በጎችዋ የተቅበዘበዙበት፣ እርስ በእርሳችን ጥላቻና ጠብን ያተረፍንበት ከባድ የፈተና ዘመናት ነበሩ። ለዚህም ዋናው ምክንያት በአንዲት ቤተክርስትያን ውስጥ ያሉ አባቶች ለሁለት መከፈላቸውና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሌላ ሦስተኛ ገለልተኛ ወገን ደግሞ መፈጠሩ ነው። በአባቶች መለያየት ምክንያት የተፈጠረው ክፍተት መናፍቃን፣ ጥቅመኞችና የፖለቲካ ሰዎች ለመለየት በሚያስቸግር መልክ በቤተክርስትያን ውስጥ እንዲሰገሰጉ አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል። ይህም ሁኔታ በአንዳንድ አገልጋዮች ዘንድ ቤተክርስትያን የተመሠረተችበትን መለኮታዊ ዓላማ እንዲስቱና የምእመናን ክርስትያናዊ ሕይወት እንዲደበዝዝ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሯል። ከዚህም በላይ ቅድስት ቤተክርስትያን በብሔራዊ ደረጃ የተፈጠሩ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የሚጠበቅባትን አዎንታዊ ሚና እንዳትጫወትም ገድቧታል። በዘመናችን ይህ የታሪክ ስብራት በመፈጸሙና ተያይዞ ለተፈጠረው ፈርጀ ብዙ ቀውስ ሰለባ መሆናችን እጅግ እንድናዝንና እንድናፍር አድርጎናል። ይህ ለዘመናት የቆየና ስር የሰደደ ችግር ከእኛ ከልጆቻችሁ ይልቅ የሚበልጠውን ኃላፊነት የተሸከማችሁ ብፁዓን አባቶቻችንን እጅግ የበለጠ እንደሚገዳችሁ መገመት አያቅተንም። አሁንም በከበራችሁበት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ተመርታችሁ፥ በብሩህ አእምሮአችሁ መክራችሁ ለወደፊቷ ቤተክርስትያን የሚበጀውን እንደምትሠሩ በሙሉ ልባችን ብናምንም ያለንበት ወቅት እጅግ ጥንቃቄ የሚያሻው ወሳኝ በመሆኑ የሚከተሉትን ሦስት ነጥቦች ከግምት ውስጥ አስገብታችሁ እንድትመለከቱ በታላቅ አክብሮትና ትሕትና እንጠይቃለን።
አንደኛ፦ ቤተክርስትያን ዛሬ ያለችበትንና የወደፊት አካሄዷን ስለማስተካከል በምትመክሩበትና በምትወስኑበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት መንግሥት በፍጹም እጁን እንዳያስገባ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ ሊከላከል ይገባል። ትላንት የተፈጸመ
Links
No signatures yet. Be the first one!
Comment