Selamena Fiker Bet 0

Letter-to-Our-Bishopic-Fathers

151 people have signed this petition. Add your name now!
Selamena Fiker Bet 0 Comments
151 people have signed. Add your voice!
1%
Maxine K. signed just now
Adam B. signed just now


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!<?xml:namespace prefix = o ns = "urn:schemas-microsoft-com:office:office" />

ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓም

 

 ለብፁዕ አቡነ ማትያስ  በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ሌቀ ጳጳስ 

ኢየሩሳሌም                                                                                                                          

 ብፁዕ አባታችን፦ ይህን ደብዳቤ የምንጽፍልዎ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስር በፓልቶክ የሰላምና የፍቅር ቤት የሚሰጠውን መንፈሳዊ አገልግሎት የምንሳተፍ በተለያዩ አገሮች የምንገኝ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምዕመናን ነን። ይህን ደብዳቤ ለመጻፍ ያነሣሣን የሌላ ወገን ተጽዕኖ ወይም ግፊት ሳይሆን የተዋሕዶ ሃይማኖታችን በጥምቀት ያገኘናት የቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ብቻ ናት።

ብፁዕ አባታችን፦ ምንም እንኳ በይፋ ባይገለጥም የተለያዩ አስተማማኝ የመገናኛ ምንጮች እንዳረጋገጡልን ፮ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው ለመመረጥ ዕጩ ሆነው እንደቀረቡ ተረድተናል። ሁሉ ነገር በተስተካከለበት ሁኔታ ቢሆን ኖሮ ይህ ደብዳቤ የደስታ መግለጫ ሆኖ እንኳን ለዚህ ክብር አበቃዎ ለማለት በተላከ ነበር። የቤተ ክርስቲያን አንድነት ለ፳ ዓመታት ያህል ለሁለትና ለሦስት ተከፋፍሎ ህልውናዋን እያናጋ ያለበት ሰዓት በመሆኑ ሹመቱን እንዳይቀበሉ ለመማጸን የምንልከው ሆንዋል። በአባቶች መካከል እርቀ ሰላም ሳይወርድ፤ የቤተክርስቲያን አንድነት ሳይመለስ ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ቢወጡ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለተጨማሪ የመለያየት ዓመታት ይዳርጋታል ብለን እንፈራለን። በመለያየት ውስጥም የፍቅር አምላክ እንደማይከብር ለብፁዕነትዎ ማስታወስ አያስፈልገንም። በእርግጥ መንበሩ ላይ ፓትርያርክ በጊዜው ባለመቀመጡ ምክንያት በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ ክፍተቶች እንደሚኖሩ እንረዳለን። ይሁን እንጂ ለዘመናት በመለያየት የኖሩ አባቶችን ማስታረቅ፣ የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና ማስተካከል፣ ምዕመናኑን በአንድ በረት ውስጥ መሰብሰብ ከምንም በላይ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ብለን እናምናለን። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከመንበር ስለ መውረዳቸውና ከሃገር ስለ መሰደዳቸው የተለያዩ ምክንያቶች ሊሰጡ ይችላሉ። ይህም ቅዱስነታቸውን በጥፋተኝነት ለመፈረጅና ብፁዕነትዎ ለፓትርያርክነት ሹመት የሚያደርጉትን ዝግጅት ትክክለኛ ነው ብሎ ለደምደም ያስችልዎ ይሆናል። ይህ ግን ለአንድ ምክንያት ሌላ ምክንያት እየሰጡ መቋጫ ወደሌለው የክርክር አዙሪት ውስጥ መግባትን እንጂ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ላለችበት ሁኔታ መፍትሔ አይሆንም፤ ችግሯንም አይቀርፈውም። የእኛ ፍላጎት ክፍት በሆነው መንበር ላይ ሌላ አባት ተቀምጦ ማየት ሳይሆን የተበላሸው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተስተካክሎ፤ በሁለት ጎራ የተከፈሉት አባቶቻችን አንድ ሆነው ማየት ነው። ይህ ሳይስተካከል ብፁዕነትዎ ሹመቱን ተቀብለው መንበሩ ላይ ቢወጡ የቤተ ክርስቲያን የመከራ ዘመን እንዲራዘም ምክንያት ይሆናሉ ብለን እንሰጋለን።

ብፁዕ አባታችን፦ እባክዎ ልጆችዎ በአባቶቻችን ተስፋ እንድንቆርጥ፤ እረኛ ያጡ ተቅበዝባዥ በጎች አያድርጉን። እባክዎ የወደፊቱን የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ከሚያጨልም ተግባር ጋር ተባባሪ አይሁኑ። እንኳን አሁን ነበልባሉ እየተንቀለቀለ ባለበት ሰዓት ቀርቶ ድሮም ሥልጣን በርቀት የሚሸሹት እሳት ነው እግዚአብሔር ካላስቻለ በቀር። በመለያየት ውስጥ ግን እግዚአብሔር ስለሌለ ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ሹመት ነው ብለን መቀበል ያዳግተናል። እባክዎ ይህን ሹመት እኛ ልጆችዎ አልወደድንሎትምና አይቀበሉ። ይቆየኝ ከቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት በኋላ ይሁንልኝ ይበሉ።

 

የብፁዕነትዎ ቡራኬ ይድረሰን

የመንፈስ ቅዱስ ልጆችዎ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን                                                            

በፓልቶክ የሰላምና የፍቅር ቤት መንፈሳዊ አገልግሎት

 

 

Links


Share for Success

Comment

151

Signatures